የሲዳማ ቡና ኣምራቾች የተሳተፉበት በቡና ጥራት ላይ የምመክር ጉባኤ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ

ሲዳም ቡና በወኢኔ
በጉባኤው ላይ የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ እና የደቡብ ክልል ኣዲሱ ፕሬዚዳንት ካላ ደሴ ዳልኬን ጨምሮ ጉዳዩ የምመለከታቸው ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

ከሃዋሳ ያገኘነው መረጃ እንደምያሳየው፤ኣገሪቱ ዘንድሮ ከ277 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለውጪ ገበያ በማቅረብ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት አቅዳለች ለዚህም ደቡብ ክልል ጨምሮ በየክክሉ የሚመረተው ቡና ጥራትና ደረጃውን ጠብቆ በብዛት መቅረብ ኣለበት ተብሏል

እንደ ኢዜኣ ዘጋባ ፤ የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ ከሲዳማ እና ከሌሎች በደቡብ ክልል ቡና አምራች ዞኖችና ልዩ ወረዳ አመራሮች ጋር ትናንት በሀዋሳ ባደረጉት ውይይት ላይ እንዳሉት ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ ዘንድሮ ለውጪ ገበያ ከሚያቀርባቸው የኤክስፖርት ሰብሎች ከ5 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለማግኘት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል

ኣክለውም ከግብርና ምርት፣ ከማኑፋክቸሪንግና ከማዕድን ዘርፎች ለመሰብሰብ ካቀደው የውጪ ምንዛሪ ውስጥ 90 በመቶ ከግብርና ምርቶች የሚገኝ መሆኑን ጠቁመው ከዚህ ውስጥ ቡና ከፍተኛውን ድርሻ እንደምይዝ ኣብራሪተዋል

2004 .169 ሺህ ቶን የታጠበና ደረቅ ቡና ለውጪ ገበያ በመላክ 832 ሚሊዮን ዶላር በ2005 .ም ከቀዳሚው ዓመት በ30 ቶን ብልጫ ያለው ቡና የቀረበ ቢሆንም በቡና ዋጋ መቀነስ ምክንያት 740 ሚሊዮን ዶላር እንደተገኘ ገልፀዋል፡፡ ዘንድሮ ቡናን በብዛት በመላክ ገቢውን ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን አስታውቀዋል። በደቡብ ክልል ከፍተኛ በቡና የተሸፈነ ማሳ ያለ ቢሆንም በአቅርቦት ማነስና በጥራት መጓደል ምክንያት የሚጠበቀውን ያህል ገቢ ማግኘት ሳይቻል እንደቆየና ይህን የአቅርቦት ውስንነትና ጥራት መጓደል በማስቀረት ለመሰብስብ የታሰበውን ገቢ ለማሳካት ርብርብ መደረግ እንዳለበት ሚኒስትሩ ገልጸዋል።


የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ በበኩላቸው እንዳሉት በክልሉ ለገበያ የሚቀርበውን ቡና ጥራቱን በማስጠበቅና በብዛት በማቅረብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ትኩረት ሰጥተው ሊረባረቡ ይገባል ብለዋል። በተያዘው ዓመት ከክልሉ ለውጪ ገበያ 124 ሺህ 103 ቶን ቡና ለማቅረብ መታቀዱን አስታውሰው ክልሉ ካለው የቡና ሽፋን አንጻር አነስተኛ በመሆኑ ይህም ዕቅዱን በመከለስ ለገበያ ለማቅረብ የታቀደውን የቡና መጠን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ህገ ውጥ የቡና ዝውውርን ለመቆጣጠር የቡና ግብይት ስርዓቱን በማጠናከር የመጀመሪያ ደረጃ የግብይት ማዕከላትን በማስፋፋት ህገውጥ ንግድን የሚቆጣጠሩ ግብረኃይሎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አጠናክረው እንዲሰሩ ማሳሰባቸውን ኢዜኣን ጠቅሶ ወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ከሃዋሳ ዘግቧል

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር