ጥቂት ስለ ጋራምባ ተራራ - ተራራው ሃዋሳ ከተማን ጨምሮ ከሌሎች የሲዳማ ከተሞች ካለው ቅርበት ኣንጻር ከመላው ዓለም የተራራ ወጪዎችን፤ የኣዕዋፍ ብሎም የተፈጥሮ ኣድናቂ ቱርስቶች መሳብ የምችል ቦታ በመሆኑ የሲዳማ ዞን መንግስት ተራራውን በፓርክነት በመከለል በቱርስት መዳረሻነት እንድለማ ብያደርገው መልካም ነው

Garamba Harbegonna, Sidama
የጋራምባ ተራራ በሲዳማ ክልል የምገኝ ትልቁ ተራራ ነው። ተራራው 9 927 ጫማ ወይንም 3 26 ሜትሪ ከፍታ ያለው ነው። እንደ ቴኣኬሪ ድረ ገጽ ዳታ ከሆነ፤ ይህ ከፍታ በደቡብ ክልል የስድስተኛ ደረጃ እንድይዝ ሲያደርገው በኢትዮጵያ ደረጃ ደግሞ 107 እንድሆን ኣስችሎታል።
በእውቁ የሲዳማ ኣርቲስት በካላ ኣዱኛ ዱሞ በተደጋጋሚ የተዘመለት የጋራምባ ተራራ እስከ ወገቡ ድረስ በኣገር በቀል ደን የተሸፈነ፤ ወሊማን በመሳሰሉ ብርቂዬ በሆኑ ኣዕዋፋት የተሞላ እና እንደ ጎሮንቴ _ ሎጊታ(ገናሌ)ን ለመሳሰሉ በርካታ ትላልቅ ወንዞች መነሻ ነው።

እንደ ትራቪሊንግ ላክ ፎር ጋራምባ ድረ ገጽ ከሆነ የጋራምባ ተራራ ከኣካባቢው ከምገኙ በርካታ ከተሞች በቀላሉ የምደረስ ሲሆን፤ ሁኔኛ የቱርዝም ሳይት መሆን የሚችል ተራራ ነው።
የጋራምባ ተራራ ሃዋሳ ከተማን ጨምሮ ከሌሎች የሲዳማ ከተሞች ካለው ቅርበት ኣንጻር ከመላው ዓለም የተራራ ወጪዎችን፤ የኣዕዋፍ ብሎም የተፈጥሮ ኣድናቂ ቱርስቶች መሳብ የምችል ቦታ በመሆኑ የሲዳማ ዞን መንግስት ተራራውን በፓርክነት በመከለል በቱርስት መዳረሻነት እንድለማ ብያደርገው መልካም ነው።
Populated Place;
a city, town, village, or other agglomeration of buildings where people live and work.
Locality;
a minor area or place of unspecified or mixed character and indefinite boundaries.
Mountain;
an elevation standing high above the surrounding area with small summit area, steep slopes and local relief of 300m or more.
Stream;
a body of running water moving to a lower level in achannel on land.
  • Goromtī Shet' (21km)
  • Gangē Shet' (29.3km)
  • Meganamo Shet' (36.6km)

    ስለ ጋራምባ  ተራራ ተጨማሪ መረጃ  ያላችሁ በምከተለው ኣድራሻ  ላኩልን እኛም ከሌሎች ኣንባቢያን ጋር እንጋራለን። 
    e-mail: nomonaoto@gmail.com  




Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር