በኣገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ እርከኖች ላይ የሲዳማ ብሄር ተወላጆች ኣሉ?

Photo from Internet
እንደምታወቀው የሲዳማ ህዝብ ካለው ከፍተኛ የህዝብ ብዛት የተነሳ በተለያዩ ጊዜያት በኣገሪቱ ህዝባዊ ስራዊት ውስጥ እየተመለመለ በፍቃደኝነት የሰራዊቱ ኣባል የምሆነው የሲዳማ ተወላጆች ቁጥር ከፍተኛ ነው። ሲዳማውያን በኣገሪቱ ጦር ሰራዊት በብዛት ከመሳተፍ ባለፈ በተለያዩ የጦር ሜዳ ውጊያዎችን ኣኩር ድሎችን በማስመዝገብ ዝና የተረፉ ናቸው።


ሲዳማውያን የኣገሪቱን ህገመንግስት በመጠበቅ ብሎም የኣገሪቱን ሎዕላዊነት በማስከበር ለህገመንግስቱ መከበር ያላቸውን የማወላዳ ኣቋም በተለያዩ ጊዚያት ኣሳይተዋል። ነገር ግን ባለፉት ኣንድ መቶ  ኣመታት ሲዳማዎች በኣገሪቱ ጦር ሰራዊት ውስጥ ያለ ማቋረጥ የተሳተፉ ሆኖ ሳለ በከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ ወይም በከፍተኛ ወታደራዊ ኣመራርነት ስማቸው የምጠቀሱ ሲዳማዎች ብዙ ኣይደሉም ምክንያቱ ምን ይሁን?ለኣብነት ያህል በኣጭር ጊዜ ውስጥ በተደጋጋሚ የኣገሪቱ መንግስት ለከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ከፍተኛ ወታደራዊ ሹመቶችን መስጠቱ የምታወስ ሲሆን፤ በእነዚህ ከፍተኛ ወታደራዊ ሹመቶች ውስጥ ምን ያህል የሲዳማ ተወላጅ ተካተው ይሁን? መረጃው ያላችው ጀባ በሉን።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር