ዋሊያዎቹ በሁሉም ረገድ መዘጋጀታቸው ተገለጸ

የእግር ኳስ ቤተሰቡም ሆነ ሙያተኞች በዋሊያዎቹ ሙሉ እምነት እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላትም ተመሳሳይ ስሜት አላቸው፡፡
ከተጨዋቾቹ አንዳንዶቹ ለናይጀሪያውያን ተገቢውን ክብር እንደሚሰጡ፣ ነገር ግን ደግሞ የመጀመሪያውን ጨዋታ በሜዳቸውና በደጋፊያቸው ፊት ማድረጋቸው ጨዋታውን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ አቅሙም ብቃቱም እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡ 
እሑድ ጥቅምት 3 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም ስለሚደረገው የኢትዮጵያና ናይጀሪያ ግጥሚያ የታላላቅ መገናኛ ብዙኃንን ትኩረት ስቧል፡፡ ናይጀሪያውያን ከዋሊያዎቹ ጠንካራ ፉክክር እንደሚጠብቃቸውም እየተዘገበ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ አቶ ሰውነት ቢሻው፣ ቡድናቸው እዚህ የደረሰው እጅግ ብዙ ፈታኝ ወቅቶችን አልፎ በመሆኑ ወደፊትም ይህ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ይገልጻሉ፡፡ ለእሑዱ ጨዋታም ቢሆንም ተጨዋቾቻቸው በሥነ ልቦናውም ሆነ በአካል ብቃቱ ዝግጁ ስለመሆናቸው በተደጋጋሚ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡ 
ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ለደቡብ አፍሪካው ዊትስ ከሚጫወተው ጌታነህ ከበደ ውጪ አዲስ ሕንፃ፣ ሽመልስ በቀለና ሳላዲን ሰይድ ዋሊያዎቹን እንደተቀላቀሉ ተነግሯል፡፡
የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ አስመልክቶ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የእግር ኳስ ቤተሰቦች በበኩላቸው፣ በዋሊያዎቹ የፀና እምነት እንዳላቸው ገልጸው ‹‹ሥጋታችን›› ሲሉ የተናገሩት፣ በአዲስ አበባ ስታዲየም ታድመው ጨዋታውን መከታተል ይችሉ ዘንድ የትኬት አሻሻጡን በተመለከተ ነው፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ካለፈው ስህተቱ እርምት ወስዶ የትኬት መሸጪያ መስኮቶች በጊዜ እንዲከፈቱና ተመልካቹም በጊዜ ትኬቱን ገዝቶ ከአላስፈላጊ መጉላላት እንዲታደጋቸው ጠይቀዋል፡፡ 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር