በሀዋሳና በሌሎች የኣገሪቱ ከተሞች የኢንዱስትሪ ዞኖችን ለመጀመር የሚያስችለው ጥናት እየተጠናቀቀ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለኢንዱስትሪ ዞንነት በተመረጡት አራት ከተሞች ላይ የኢንዱስትሪ መንደር ለማቋቋም የሚያስችለው ጥናት እየተገባደደ ነው ተባለ።
የኢንዱስትሪ ሚንስትር አቶ አህመድ አብተው እንዳሉት ፥   በአዲስ አበባ ድሬድዋ ፣ ሀዋሳና ኮምቦልቻ ሊገነቡ የታቀዱትን የኢንዱስትሪ ዞኖች  ለመጀመር የሚያስችለው ጥናት እየተጠናቀቀ ነው።
ከጥናቱ በተጓዳኝ መንደሩን ለመገንባት የሚያስችለውን ገንዘብ የማፈላለግ ሰራም እየተካሄደ ነው።
በዚህ መሰረት ከአንድ የእስራኤል ድርጅት ጋር በኮምቦልቻ የሚገነባው የኢንዱስትሪ መንደር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን ነው ሚነስትሩ የተናገሩት።
በተመሳሳይ በአዲስ አባባ ለሚ ሳይት ከተገነባው በተጨማሪ ሌላ የኢንዱስትሪ መንደር ለመገንባትም ከአለም ባንክ ጋር ንግግር ተጀምሯል።
በድሬድዋና በሃዋሳ ለሚገነቡት የኢንዱሰትሪ መንደሮችን ከመንግስት ጋር በመተባባር የመገንባት ፍላጎት  ያላቸው ድርጅቶችም የአዋጭነት ጥናት እያደረጉ ነው ተብሏል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር