በንብ ማነብ ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ከ44 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኙ

ሃዋሳ መስከረም 12/2006 በሲዳማ ዞን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብ ማነብ ስራ የተሰማሩ ከ58 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ከ44 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ፡፡ በመምሪያው የግብርና ልማት እቅድ የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ ደርቤ በትራ ሰሞኑን እንደገለጹት አርሶአደሮቹ ገቢውን ያገኙት 888 ሺህ ኪሎ ግራም ማር ለገበያ በማቅረብ ነው፡፡ በንብ ማነብ ሥራው ላይ ከተሰማሩ አርሶ አደሮች መካከል 25 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ የማር ምርቱ የተገኘው 35 ሺህ ከሚጠጉ ባህላዊ ቀፎዎች፣ ከ4 ሺህ በላይ ከሚሆኑ የሽግግር ቀፎዎችና 378 ዘመናዊ ቀፎዎች መሆኑን ጠቁመው በበጀት ዓመቱ በስራ ላይ የዋለው የቀፎ ቁጥርና የተገኘው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ሰባት በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልፀዋል፡፡ በዞኑ ለገበያ የሚቀርበው የማር ምርት በየዓመቱ ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ መምጣቱን የገለጹት ኦፊሰሩ በእድገትና ትራስፎርሜሽን እቅድ ዘመን መጨረሻ ከማር ምርት ተጠቃሚ የሚሆኑት አርሶ አደሮች ቁጥር ሊያድግ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም በተያዘው ዓመት ለገበያ የሚቀርበውን የማር ምርት በሶስት እጥፍ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ኃላፊው ጨምረው አሰታውቀዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=12011&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር