የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ጥቅምት 16 /2006 ይጀመራል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የፕሪሚየር ሊግ እና የብሔራዊ ሊግ ክለብ ተወካዮች በተገኙበት በክለቦች መተዳደሪያ ደንብና የዲስፕሊን መመሪያዎች ማሻሻያ ላይ ዛሬ ነሐሴ 29/2005 በኢትዮጵያ ሆቴል ውይይት አካሄደ፡፡
የፌደሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ በመተዳደሪያ ደንቡና በዲስፕሊን መመሪያው ያቀረባቸው ማሻሻያዎች ተገቢ መሆናቸውን የየክለቦቹ ተወካዮች ተናግረዋል፡፡
የተሸሻለው መመሪያ በጠቅላላ ጉባኤው ፀድቆ በስራ ላይ ሲውል በባለፉት ዓመታት በውድድሩ የተከሰቱ ችግሮችን እንደሚቀርፍ እምነታቸው መሆኑን የየክለቦቹ ተወካዮች ገልፀዋል፡፡
በሀገር ውስጥ የተጨዋቾች ዝውውር መንግስት እያጣው ያለው ግብር በተሻሻለው የዲስፕሊን መመሪያ ላይ እንደሚስተካከልም ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክለቦች የ2006 የውድድር ዘመን ጨዋታ የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓትም በእለቱ ተካሂዷል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ መርሃ ግብር ጥቅምት 16 የሚጀምር ሲሆን በመጀመሪያው ሳምንት ደደቢት ከኢትዮጵያ ቡና የተገናኙበት ጨዋታ ከወዲሁ ትኩረትን ስቧል፡፡
ደደቢት በ2005 የውድድር ዘመን ፕሪሚየር ሊጉን 1ኛ በመሆን ያጠናቀቀ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና ሶስተኛ ሆኖ መጨረሱ ይታወሳል፡፡
በመጀመሪያው ሳምንት ሌሎች ጨዋታዎች ሙገር ሲሚንቶ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ዳሽን ቢራ ከሀረር ቢራ፣ ኢትዮጵያ መድህን ከአርባ ምንጭ፣ መከላከያ ከሲዳማ ቡና፣ ሐዋሳ ከነማ ከመብራት ሃይል እንዲሁም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወላይታ ዲቻ ይገናኛሉ፡፡
የዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ የውድድር መርሃ ግብር ዓለም አቀፋዊ ውድድሮቹንና ስታንዳርዱን ጠብቆ የተሰራ በመሆኑ በ2005 የነበረውን የሊጉ የጨዋታ መቆራረጥ ያስተካክላል ተብሏል፡፡
የተለያዩ የዓለም ሀገራት የወዳጅነትና የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን በሚያደርጉበት ወቅትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በተመሳሳይ መካፈል እንዲችል የሊጉ የውድድር መርሃ ግብር ተስተካክሏል ተብሏል፡፡
ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው የጨዋታ መርሃ ግብር ተግባራዊ ባለማድርጉ ብሔራዊ ቡድኑ ለመካከለኛው አፍሪካ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት የሚረዳ የወዳጅነት ጨዋታ ማድረግ አለመቻሉ ይታወሳል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር