በመኸር እርሻ ሥራ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደገ እየሰሩ መሆናቸውን በሲዳማ ዞን የጐርቼ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ፡፡

በወረዳው በ2ዐዐ5 እና በ2ዐዐ6 ዓ/ም የመኸር እርሻ ከ3 ሺህ 57ዐ  ሄክታር በላይ መሬት በዋና ዋና ሰብሎች ዘር ለመሸፈን ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡፡
አርሶ አደር አመሎ ኪቦ አና አርሶ አደር ቀጤ ወጀቦ በወረዳው የሐርቤ ሚቀና ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ የመኸር እርሻ ሥራን ውጤታማ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ገልፀው በተለያዩ ጊዜያት ባገኙት የክህሎት ሥልጠና በመጠቀም ጥምርታቸውን በጠበቀ መልኩ በመዝራት ላይ እንዳሉ ተናግረዋል፡፡
የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ስጦታው ከንባታ በበኩላቸው በ2ዐዐ5 እና በ2ዐዐ6 ዓ/ም የመኸር እርሻ ከ3 ሺህ 57ዐ ሄክታር በላይ መሬት በዋና ዋና የሰብል ዘሮች ለመሸፈን የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝና እስከ አሁንም 3 መቶ 36 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈናቸውን ገልፀዋል፡፡
በመኸር እርሻ በዘር ከሚሸፈን ማሳ አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል ሲል የዘገበው የወረዳው የመንግሰት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው፡፡
ምንጭ፦http://www.smm.gov.et/_Text/13NehTextN805.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር