በሲዳማ ዞን ጐርቼ ወረዳ የሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲ እውን ለማድረግ ከ12 ሺህ በላይ ችግኝ ተክለዋል፡፡

በችግኝ ተከላው የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰንበቱ ተካ የአረንጓዴ ልማት ቀያሽ ከሆኑት ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተር የተጀመሩ ልማቶችን ለማስቀጠል ህዝቡና አመራሩ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ህብረተሰቡም  በችግኝ ተከላውና በፓርክ ምስረታው ላይ ያሳየውን ቁርጠኝነት በእንክብካቤ ስራው ላይም አጠናክሮ ሊቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡
በችግኝ ተከላው ወቅት ያነጋገርናቸው አንዳንድ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርን የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ለማሳካት የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል፡፡
በወረዳው በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስም በሁሉም ቀበሌያት ፓርኮች ተቋቁመዋል ከ12 ሺህ በላይ ችግኞችም ተተክለዋል ሲል የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዘግቧል፡፡
የዞኑ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ አሸብር ልሳኑ በበኩላቸው ከፓርኩ የሚገኘው ገቢ በዚሁ አካባቢ ለሚገኙ ማህበረሰቦች የተለያዩ የመሰረተ ልማት አውታሮች እንደሚሟሉበት ተናግረው  ህብረተሰቡ ፓርኩን በባለቤትነት እንዲቆጣጠርም ጭምር አሳስበዋል፡፡
በዚሁ ዙሪያ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በተደረገ ውይይት ፓርኩ የማንም ሳይሆን የራሳችን በመሆኑ ከዚህ በኃላ የሚፈጠረውን ጥቃት ለመከላከል ወንጀለኞችን አሳልፈን ለህግ እንሠጣለን ሲሉ የሀገር ሽማግሌዎች ተናግረዋል፡፡ የደቡብ ኦሞ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አንደዘገበው፡፡
ምንጭ፦http://www.smm.gov.et/_Text/13NehTextN705.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር