በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ለሙስና ኮሚሽን ጥቆማ ቀረበ ተባለ


ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ በደቡክ ክልል ፕሬዚዳንት በነበሩበት ጊዜ በቤተሰቦቻቸው እና በሃዋርያት ቤተክርስቲያን መሪዎች ስም በመሬት ቅርሚያ እና ችብቸባ ስራ ላይ ተሰማርተው ነበር ሲሉ አንድ ከአዋሳ ግለሰብ የመጡ ማስረጃቸውን አያይዘው ለሙስና ኮሚሽን ጥቆማ መስጠታቸውን አንዲት በኮሚሽኑ ውስጥ የሚሰሩ ግለሰብ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::ግለሰቧ እንዳሉት ወደ ኮሚሽኑ የመጡት ሰው የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አማካሪ የነበሩ ሲሆንጥቆማውን እና ማስረጃቸውን የተቀበሏቸው በቀጠሮ ኮሚሽነር አሊ ሲሆኑ ለረዥም ሰአት ተነጋግረዋል::

በአቶ ሃይለማርያም ላይ የመጣው ጥቆማ እንደሚያመለክተው ብስልጣናቸው ተጠቅመው በኢናታቸው እና በአባታቸው ቤተሰቦች ስም እንዲሁም በቤተ ክርስቲያን መሪዎች ስም ለተለያየ ጊዜ መሬቶችን በመውሰድና በመሸጥ ሰፋፊ እርሻዎችን በመያዝ የቡና እና የፍራፍሬ ተክሎችን ወደ ኬንያ በኮንትሮባንድ በመላክ የኢትዮጵያን ድንበር ተገን በማድረግ በህገወጥ ንግድ እና የመሳሪያ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች ከለላ በመስጠት የተለያዩ ስኮላርሺፖችን በማስመጣት እና በመሸጥ እንዲሁም ከትግሬ ጄኔራሎች ጋር በመተባበር የሃሰት ሰንዶችን በማዘጋጀት የመንግስት እና የህዝብ ንብረቶችን ዘርፎ በማዘረፍ የሚሉ እና ተመሳሳይነት ያላቸው ጥቆማዎች እንደተሰጡ ግለሰቧ ገልጸዋል::
አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች በሃዋርያት ቤተክርስቲያን ስም የራሳቸውን ህንጻ ገንብተዋል እየገነቡም ነው ለመገንባትም የታሰቡ ፕሮጀክቶች አሉ የሚል ተደራራቢ የህንጻ ግንባት ጥቆማ ተደርጎባቸዋል::
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሃዋርያት ቤት ክርስቲያን አቶ ሃይለማርያምን እና ሌሎች ባለስልጣናትን ተገን በማድረግ በሙስና መጨማለቋን እኚሁ ግለሰብ ከሰጡት ጥቆማ ጋር የተገለጸ ሲሆን ቤተክርስቲያኒቷ ላለፉት ጊዜያት በስሟ ከውጭ ሃገራት የሚገቡ ኮንቴነሮች እና የታሸጉ ካርቶኖች እንዳይፈተሹ አቶ ሃይለማርያም ትእዛዝ ይሰጡ እንደነበር ተጠቁሟል::መሪዎቿ በደቡብ ባለስልጣናት መመሪያ ብቻ የደሃውን መሬት እየነጠቁ በመከፋፈል ህዝብን እያስለቀሱ መሆኑን ይሄው ጥቆማ ያስረዳል::
ምንጭ፦http://www.ethiopianreview.com/forum/viewtopic.php?f=25&t=56266

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር