የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሶስት ፖለቲካ ፓርቲዎች አገደ

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ደንብን ተላልፈው በመስራት አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን  አስታወቀ፡፡
ቦርዱ የ 11 ወራት የስራ አፈጻፀም ሪፖርቱን  ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው የፖለቲካ ድርጅቶቹ ህግን ተላልፈው አግኝቻቸውለሁ በሚል  ቦርዱ እርምጃ መውሰዱን ያስታወቀው፡፡

በዚህ መሰረትም የኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ( ኦነፓ)፡የኢትዮጵያ ፓን ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኢፖኦፓ)፡የኢትዮጵያ ሱማሌ ልማት ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኢሱልዴፓ) የታገዱ ሲሆን የሸኮና አካባቢው ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ሾአህድድ) የመጨረሻ ማስጠንቀቅያ እንደተሰጠው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንደተናገሩት ሶስት አዳድስ የፖለቲካ ፓርቲዎች  እውቅና ተሰጥተዋል፡፡አንድ የግንባር እና የውህደት ጥያቄዎችም አዎንታዊ ምላሽ እንዳገኙም ገልጸዋል፡፡

በ2005 በተካሄደው የአካባቢ፣ የአዲስ አበባና የድሬደዋ ከተሞች ምክርቤቶች ምርጫ የሴቶች ተሳትፎ 48 በመቶ መደርሱም በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡

ቦርዱ ለምርጫው ማስፈጸሚያም ከአራት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ጥቅም ላይ አውሏል፡፡

ከቀረበው ሪፖርት በመነሳትም የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት  አባላት ለነሷቸው  የተለያዩ ጥቄዎች ቦርዱ ምላሽ ሰጥል፡፡ በዚህም ቦርዱ በአመቱ ለመስራት አቅዶ ያልተገበረው  የዳታ ቤዝ መረጃ አያያዝ ስርአት በአፋጣኝ ሊተገበር እንደሚገባ  ምክርቤቱ አሳስቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር