የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛው ስብሰባውን ዛሬ ግንቦት 3/2005 ዓ.ም እያካሄደ ነው፡፡
ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በዚሁ ስብሰባው በያዝነው አመት የተሰሩ በክልሎች የከተማና የገጠር ሪፖርት እንዲሁም የገጠር እና የከተማ ሱፐርቪዥን ሪፖርት ላይ ይወያያል፡፡
ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በአጀንዳው ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል በሚያዝያ ወር በተካሄደው የአዲስ አበባ ምክር ቤትና የአካባቢ ምርጫ አፈጻጸምን በተመለከተ ይመክራል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በ9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የተላለፉ ውሳኔዎችን ወደ አባላት እና ወደ ተለያዩ አካላት ለማድረስና ውሳኔዎቹን ተግባራዊ ለማድረግ በቀጣይ ሁለት አመታት የሚከናወኑ መሰረታዊ ተግባራቶችን ይዳስሳል፡፡ በወቅቱ ከቤቱ በሚነሱ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን በማሳለፍ ስብሰባውን ያጠቃልላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ-የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ምክር ቤት ፅ/ቤት

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር