በሲዳማ ዞን ከአንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ በጀት የገጠር ቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ በመካሄድ ላይ ነው

አዋሳ ሚያዚያ 10/2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ከአንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ በጀት ከአንድ ሺህ 500 ኪሎ ሜትር በላይ የገጠር ቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ መሆኑን የዞኑ መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ገለጸ፡፡ በፕሮግራሙ ከ12 ሺህ ለሚበልጡ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል መፈጠሩ ተገልጿል፡፡ የመምሪያው ሀላፊ አቶ ማቴዎስ ዳንኤል ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገጹት ሀገራዊና ክልላዊ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ተከትሎ በዞኑ ሁሉንም የገጠር ቀበሌዎች ደረጃቸውን በጠበቁና ክረምት ከበጋ በሚያገለግሉ መንገዶች በማገናኘት የህብረተሰቡን አስተዳደራዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ፕሮግራሙ በዞኑ በከተማና በገጠር፣ በአምራችና በአገልግሎት ሰጪው እንዲሁም በግብርናና በኢንዱስትሪ ዘርፎች መካከል የሚኖረውን ትስስር በማጠናከር አርሶ አደሩ ምርቶቻቸውን ለገበያ በማቅረብ ከምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ በዞኑ እስካሁን 927 ኪሎ ሜትር የገጠር ቀበሌዎችን ክረምት ከበጋ የሚያገለግል መንገድ መኖሩን ጠቁመው በያዝነ ዓመት ለዘረፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሽፋኑን ከፍ ለማድረግ የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ በመካሄድ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ ከዞን ጀምሮ እስከ ቀበሌ በተደረገ ሁለገብ ርብርብ እስከሁን 262 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ቀሪውን እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ለማጠናቀቅ ከአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የቅየሳ ፣ የዲዛይንናና የአፈር ድልዳሎ ስራ ሙሉ በሙለ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ የቀበሌ ተደራሸ መንገድ ግንባታ ፕሮግራም 25 በመቶ በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሸፈን በመሆኑ ከ154 ሺህ በላይ ህዝብ 850 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የጠረጋና ምንጣሮ ስራ ማከናወኑን ገልጸው በዚህም ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ ከወጪ ማዳኑን ገልፀዋል፡፡ በፕሮግራሙ ከተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎቸ መካከል 31ሺህ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ብለዋል፡፡ ትራንስፖርት በዞኑ እየተመዘገበ ላለውና በቀጣይነት ይመዘገባል ተብሎ ለሚገመተው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ መምሪያው የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ ፕሮግራም ወጤታማ እንዲሆን ከ57 በላይ አማካሪዎችና አነስተኛ የስራ ተቋራጮችን አደራጀተው በማሰልጠን ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡ ድህነትን ለመቀነስ የሚሊኒየሙን የመሰረተ ልማት ግቦችን የማሳካትና ተደራሽነትን ለሁሉም ዜጎች ማዳረስ ቀዳሚ ተግባር በመሆኑ ዞኑ በመሉ አቅም በመረባረብ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ ፕሮግራም ከመንገድ ተደራሽነት ዓላማው ጎን ለጎን የስራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ ባለፈው ዓመት በዘረፉ ከ6ሺህ 400 ለሚበልጡ ዜጎች በተያዘው በጀት ዓመትም ከ12 ሺህ ለሚበልጡ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡ በዞኑ በመገንባት ላይ የሚገኘውን የገጠር ቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ ስራ በሙሉ በተቀመጠው ጊዜ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማብቃት የተቀናጀ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ያስታወቁት ሃላፊው ከበጀት በተጨማሪ የከልሉ መንግስት ዘጠኝ ከባድ ማሽነሪዎችን ጨምሮ ለግንባታው የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች መስጠቱን ገልፀዋል፡፡ በዞኑ 19ኝ ወረዳና ሁለት የከተማ አስተዳደር የሚገኙ 528 የገጠር ቀበሌዎችን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ከዋና መንገድ ጋር ለማገናኘት ከ2ሺህ 500 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ግንባታ እንደሚከናወን አቶ ማቴዎስ ተናግረዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=7127&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር