የአለም የጤና ድርጅት የአዕዋፍ ኢንፉሌንዛ ከሰው ወደ ሰው ስለመተላለፉ መረጃ አላገኘሁም አለ


አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የአእዋፍ ኢንፉሌንዛ ቻይና ውስጥ መከሰቱ የተሰማው ባሳለፍነው ሳምንት ነው።
ከአእዋፍ ወደ ሰው በመተላለፍ እስከ አሁን የሁለት ሰዎች ህይወትን አጥፍቷል ፡፡
በቻይና የአለም የጤና ድርጅት ተወካይ እንዳሉት ከሆነ ፥ ከበሽታው ተጠቂዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት በነበራቸው 80 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ በበሽታው እንዳልተያዙ ለማረጋገጥ ተችሏል ፡፡
ኤች ሰባት ኤን ዘጠኝ ተብሎ የተሰየመው ይህ ቫይረስ እስካሁን  ክትባትም ይሁን መድሃኒት አልተገኘለትም፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር