የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በመጪዎቹ ግንቦትና ሰኔ የሙከራ ምርት ይጀምራል


አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በመጪዎቹ ግንቦትና ሰኔ የሙከራ ምርት የሚጀምር ሲሆን ፥ ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅም ሶስቱ ነባር የስኳር ፋብሪካዎች ከሚያመርቱት በ2 እጥፍ የሚበልጥ ምርት እንደሚያስገኝ የስኳር ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ።

የተንዳሆ ስኳር ልማት ፋብሪካ ከእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ በፊት ሊጠናቀቅ ባለማቻሉ በእቅድ ውስጥ እንዲካተት የተደረገ ነው።
በመጠናቀቅ ላይ ነው የሚገኘው የዚሁ ፋብሪካ የመስኖ ልማትም በውሀና ኢነርጂ ሚንስቴር ነው የተሰራው ሲሆን ፥ በአሁኑ ወቅት ግድቡ ተግንብቶ ውሀ እንዲይዝ ተደርጓል ፣ ከ42 ኪሎሜትር በላይ የዋና ቦይ ዝርጋታም ተከናውኗል።
ለስኳር ምርት ዋና ግብአት የሆነው የሸንኮራ አገዳ ልማትም ተከናውኗል ፥ በዚህም መሰረት ከ8 ሺህ ሄክታር በላይ የተተከለው የሸንኮራ አገዳ በጥሩ ሁኔታ እያደገ ነው ብለዋል በኮርፖሬሽኑ የዋና ዳይሬክተር አማካሪና የህዝብ ግንኙነት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዲንጋሞ።
ፋብሪካው በመጀመሪያው ዙር 13 ሺህ ቶን ሸንኮራ በቀን በመፍጨት ነው ማምረት የሚጀምር ሲሆን ፥ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ደግሞ ቀደም ካሉት 3 ፋብሪካዎች ሁለት እጥፍ ሸንኮራ ይፈጫል ነው የተባለው።
በአሁኑ ወቅት የፋብሪካው የመጀመሪያ ደረጃ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ያለ ሲገኝ ፥  ከሁለት ወራት በኋላ ደረጃ በደረጃ ወደ ምርት ይሸጋገራልም ነው ያሉት አቶ አስፋው ።
ይህኛው እያመረተ የሁለተኛው ዙር ግንባታ ሲጠናቀቅም በቀን26 ሺህ ቶን ሸንኮራ ወደሚፈጭበት ደረጃ ይደርሳል ብለዋል ።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር