በሃዋሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የባህል ፌስቲቫልና የኢንዱስትሪ ሳምንት ተጠናቀቀ

ተፈጥሮአዊ መስህቦችና ባህላዊ ቅርሶች ለሀገሪቱና ለዓለም ህዝቦች በማሳወቅ ለገፅታ ግንባታው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው  እየሰራ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በሃዋሳ ከተማ ለአምስት ቀናት  ሲካሄድ የቆየው የባህል ፌስቲቫልና የኢንዱስትሪ ሳምንት መጋቢት 30/2005 ተጠናቋል፡፡
በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ኢንዱስትሪ የልማትና የትብብር ዳይሬክቶሬት ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ ተስፋዮ ኦታንጎ በፌስትቫሉ መዝጊያ ላይ እንደገለጹት የብዝሃ ባህል፣ የቅርስና የተፈጥሮ መስህቦችን ቀጣይነት ባለው መልኩ በመጠበቅና በማልማት የህዝቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጎልበት እየተሰራ ነው፡፡
የሀገሪቱን ዕምቅ የባህል፣ የተፈጥሮ ቅርሶችና ዕሴቶችን በተገቢው መንገድ በማልማት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ጉልህ ድርሻ እንዲኖራቸው ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አቶ ተስፋዬ ለሁለተኛ ጊዜ ከመጋብት 25  እስከ መጋቢት 30 ቀን 2005 ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ በተካሄደው የባህል ፌትቫልና የኢንዱስትሪ ሳምንት ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ ከዘጠኙም ክልሎች የመጡ የባህል ቡድኖች የየአከባቢያቸውን ባህልና እሴቶችን በአደባባይ በማሳየት ባህል ለአንድነት፣ ለሰላም፣ ለልማት፣ ለዕውቀትና ለመልካም ገፅታ ግንባታ ያለውን ጠቀሜታ አጉልተው ያሳዩበት መድረክ ነበር ብለዋል፡፡
ከትግራይ፣ ከኦሮሚያ፣ ከአማራና ከአዲስ አባባ የመጡ አንዳንድ የባህል ልዑካን ቡድን አባላት በሰጡት አስተያየት ፌስትቫሉ የእርስ በርስ ግንኙነትን የሚያጠናክር፣ ለዕውቀት ሽግግር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ከመሆኑም ባሻገር ክልሎች የየራሳቸውን ዕምቅ የባህል ሃብቶቻቸውን ለማስተዋወቅና መልካም ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ እንደረዳቸው ተናግረዋል፡፡
''የባህልና ቱሪዝም ሃብቶቻችንን በማልማት የመለሰን ራዕይ እናሳካለን'' በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የሰነበተው ፌስትቫል  2006 የጎንደር ከተማ እንድታዘጋጅ በመምረጥ መጋቢት 30/2005 ማምሻውን መጠናቀቁን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር