ለመሆኑ ያለተፎካካሪ የተደረገው የሲዳማ ምርጫ ውጤት ኣሽናፊዎቹን ጩቤ ያስረግጥ ይሁን?

ደኢህዴን ያለምንም ተፎካካሪ የተወዳደረበት የቀበሌ ምክር ቤት ምርጫ ውጤት ይፋ ሆኗል። የምርጫው ውጤት ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ጀምሮ የሚታወቅ ሲሆን ለፎርማሊት ተብሎ ውጤቱ ይፋ ተደርጓል ይለናል የኢዜኣ ዘጋባ። ለመሆኑ ያለተፎካካሪ የተደረገው የሲዳማ ምርጫ ውጤት ኣሽናፊዎቹን ጩቤ ያስረግጥ ይሁን? ለማንኛውም የምርጫ ውጤ ይፋ መደረጉን የተመለከተ ዜና ከታች ያንቡ።

አዋሳ ሚያዚያ 14/2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ትናንት በተካሄደው የቀበሌ ምክር ቤት ምርጫ ለመራጭነት ከተመዘገበው ህዝብ ከ93 በመቶ በላይ መሳተፉን የዞኑ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ዱካሞ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹ በዞኑ አንድ ሺህ 507 የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣጡ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቆ ጊዜያዊ ውጤቱ ይፋ ሆኗል፡፡ በዞኑ 19 ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደር ከተመዘገው አንድ ሚሊዮን 116ሺህ በላይ መራጭ 93 በመቶ ድምፅ ድምፅ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያ ሃላፊዎች፣ የህዝብ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች በሰጡት አስተያየት ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መካሄዱን ገልፀዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር