ሲዳማን ጨምሮ በመላው ኣገሪቱ ስለምርጫው አጠቃላይ ሂደት ገለፃ ሊደረግ ነው

ሚያዝያ 6 እና 13 ለሚካሄደው የአካባቢ፣ የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ምክር  ቤቶች ምርጫን አስመልክቶ  መጋቢት 27/2005 ስለምርጫው አጠቃላይ ሂደት በየምርጫ ጣቢያው ገለፃ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
የቦርዱ የህዝብ ግኑኙነት ምክትል ሃላፊ አቶ ይስማው ጅሩ  ሕብረተሰቡ በምርጫው ዕለት መደናገር እንዳይፈጠርበት በድምፅ አሰጣጡ ዙርያ ከወዲሁ ግንዛቤ እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ምርጫው የሚጀመርበትንና የሚጠናቀቅበትን ሰዓት፣ በምርጫው ዕለት መራጮች ምን ማድረግ እንደሚገባቸውና ሌሎች ለድምፅ አሰጣጡ የሚያግዙ አስፈላጊ መረጃዎችን እንዲያገኙም ገለፃው አስፈላጊ ነው ያሉት ሃላፊው ሕብረተሰቡም በስፍራው በመገኘት አጠቃላይ ሁኔታውን በመረዳት በእውቀት ላይ የተመሰረተ ድምጽ እንዲሰጥ የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ የሚዲያ ባለሞያዎች ምርጫው ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒ እንዲሆን ቁልፍና ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ቦርዱ ገልጿል፡፡
የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግኑኙነት ምክትል ሃላፊ አቶ ይስማ ጅሩ ምርጫው የተሳካ እንዲሆን የሚዲያ ባለሞያዎች የወጡትን የምርጫ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በማስፈፀም ረገድ ከፍተኛ ሃላፊነት አለባቸው ብለዋል፡፡
ሚያዚያ ስድስት ለሚጀመረው የከተማና የአካባቢ ምርጫ የሚሆን ቁሳቁስ አዲስ አበባን ሳይጨምር ለሁሉም ክልሎች መዳረሱን ቦርዱ ጠቁሟል ሲል ኢዜአ ዘገቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር