ሲዳማን ጨምሮ የሸማቾችን ቅሬታ የሚሰብሰብ የነጻ የስልክ መስመር በስራ ላይ ዋለ
የንግድ አሰራርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የሸማቹን ህብረተሰብ ቅሬታ ለመሰብሰብ የሚያስችል አዲስ የነጻ የስልክ መስመር ጥሪ በስራ ላይ ማዋሉን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ የሸማቾች ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ ግርማ አለማር መጋቢት 26/2005 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ የሸማቹን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ የሚረዳ 8478 የመስመር ቁጥር ያለው ነጻ ጥሪ ከመጋቢት 26/2005 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ ውሏል ብለዋል፡፡
ይህም በአገሪቱ በማንኛውም አካባቢ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን የንግድ ስርዓቱ በህግ አግባበ ለመዳኘት የሚሰራውን ስራ ለማጠናከር እንደሚረዳ አብራርተዋል፡፡
መስመሩ በአንድ ጊዜ አራት ጥሪዎችን መቀበል የሚያስችል ሲሆን ህብረተሰቡም በነጻ የስልክ መስመሩ በመጠቀም በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚደርስባቸውን የመብት ጥሰትና የጸረ ንግድ ውድድር ተግባራት ሲፈጸም ጥቆማ ለማድረስ እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ሸማቹን ለጤና መታወክ የሚዳርጉ ምርቶች በገበያ ሲያጋጥማቸው በነጻ የስልክ መስመሩ ለባለስልጣኑ ቢጠቀሙ ተገቢውን ምላሽ ያገኛሉ ብለዋል፡፡
ምንጭ ፋና ብሮድካስት
Comments
Post a Comment