የምርጫ ዝግጅትና ተቃዉሞዉ በኢትዮጵያ፤ የሲዳማ አርነት ንቅናቄም በምርጫዉ እንደማይታፍ አስታዉቋል።


ኢትዮጵያ ዉስጥ የመፊታችን ዕሁድ እና በሳምንቱ ዕሁድ በሚደረገዉ አካባቢ ምርጫ ከሠላሳ-አንድ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፁን ለመስጠት መመዝገቡን የሐገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙት ሠላሳ ሰወስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ግን በመጪዉ ዕሁድ በሚጀምረዉ አካባቢያዊ ምርጫ ላለመሳተፍ ወስነዋል።
ኢትዮጵያ ዉስጥ የመፊታችን ዕሁድ እና በሳምንቱ ዕሁድ በሚደረገዉ አካባቢ ምርጫ ከሠላሳ-አንድ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፁን ለመስጠት መመዝገቡን የሐገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የቦርዱ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ይስማ ጅሩ እንደገለጡት በሁለት በተከፈለዉ ምርጫ ሃያ-አራት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የወከሉ ከስድስት ሚሊዮን በላይ እጩዎች ይወዳደራሉ። የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር አቶ ይስማ ጅሩን አነጋግሯቸዋል።የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙት ሠላሳ ሰወስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ግን በመጪዉ ዕሁድ በሚጀምረዉ አካባቢያዊ ምርጫ ላለመሳተፍ ወስነዋል።ፓርቲዎቹ እራሳቸዉን ከምርጫዉ ያገለሉበትን ምክንያት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ማስረዳታቸዉን አስታወቀዋል።የጋራ ትብብር የመሠረቱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረቡት ቅድመ-ሁኔታ ካልተሟላ በምርጫዉ እንደማይሳተፉ በተደጋጋሚ አስታዉቀዉ ነበር። የጋራዉ ትብብር መሪዎች እንዳሉት ይሕን ምክንያታቸዉን ሠሞኑን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገልፀዋል። በተመሳሳይ ዜና የሲዳማ አርነት ንቅናቄም በምርጫዉ እንደማይታፍ አስታዉቋል። የንቅናቄዉ ባለሥልጣናት እንደሚሉት አባላቶቻቸዉና ደጋፊዎቻቸዉ ይታሰራሉ፥ ይሸማቀቃሉም። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር