የአለታ ወንዶ ወረዳ ሴቶች ለምርጫው መዘጋጀታቸውን ገለጹ

አዋሳ መጋቢት 09/2005 በመጪው ሚያዚያ ወር በሚካሄደው የዞን፣ የወረዳና ቀበሌ ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ በንቃት ለመሳተፍ መጋጀታቸውን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ሴቶች ገለጹ፡፡ ከወረዳው ሴቶች መካከል አንዳንዶቹ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በምርጫው መብትና ጥቅማቸውን የሚያስከብርላቸውን ለመምረጥ ከወዲሁ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ በተለይ የወረዳው ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጽሕፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ አዛለች ካያሞ እንዳስረዱት በአለታ ወንዶ 29 የገጠርና ከተማ ቀበሌዎች ለምርጫው ከተመዘገበው 59ሺህ ያህል ህዝብ ግማሽ ሴቶች ናቸው፡፡ በተመራጭ፣በአስመራጭና ታዛቢነት ከወንዶች እኩል ስብጥርና ተሳትፎ እንዳላቸው አስታውቀው በመራጭነትና በተመራጭነት የተመዘገቡት ሴቶች በስርዓቱ ያገኙትን ተጠቃሚነት ዘላቂ ለማድረግ ሰርተው የሚሰሩ ተወካዮቻቸውን ለመምረጥ እለቱን በጉጉት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ በድርጅት ለወረዳ ምክር ቤት በዕጩነት ከቀረቡት መካከል ወይዘሮ አልማዝ ዲንጋሞ ቢመረጡ ሴቶች ከወንዶች እኩል ሆነው በማህበራዊ ፣ በኢኮኖሚና ፓለቲካ ያላቸውን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ጠንክረው ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡ በድርጅታቸው ተወክለው ለምርጫው ተሳታፊ በመሆናቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡ በመራጭነት ከተመዘገቡት መካከል ወጣት አሰለፈች በቀለና እመቤት ተሰማ ሴቶች ለዘመናት ሲደረስባቸው ከነበረው የጾታ ተጽዕኖናና ጭቆና ተላቀው ባገኙት መብት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቀው በቀጣዩ ምርጫ በንቃት በመሳተፍ ጥቅሞቻቸውን የሚስጠብቁላቸውን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል፡፡ የወረዳው ምርጫ ጽሕፈት ቤት አስተባበሪ አቶ ወርቁ አኔቦ እንደገለጹት ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዘቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅንቄ ሌላ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ለዞን ምክር ቤት አምስትና ለወረዳ ምክር ቤት ደግሞ 86 ዕጩዎች ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=6429

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር