9ኛው የኢህአዴግ ጉባዔ ተጠናቀቀ
ከመጋቢት 14 እስከ 17/2005 ዓ.ም በባህርዳር ሲካሄድ የሰነበተው ኢህአዴግ 9ኛው ጉባኤ ዛሬ መጋቢት 17/2005 ተጠናቀቀ፡፡
ጉባኤው የተጠናቀቀው የአቋም መግለጫ በማውጣትና የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን በመምረጥ ነው ፡፡
9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ሲጠናቀቅ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡ የሚከተሉት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
Ø በተሃድሶ እንቅስቃሴና በሂደት የጎለበተው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመራችን በትክክለኛ መንገድ እየሄደ ነው፡፡
Øየልማት ሃይሎችን በተደራጀ መልኩ በመምራት እስከአሁን አሟጠን ያልተጠቀምናቸው እድሎች በመጠቀም ህዳሴያችን ለማሳካት እንረባረባለን፡፡
Ø በልማት ሰራዊት ግንባታ የሚታዩት ጉድለቶች በመፍታት የግብርና ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የዋጋ ግሽበትን በመቀነስና የህዝባችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንሰራለን፡፡
Ø በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ልማታዊ ሰራዊት በተጠናከረ መልኩ በመገንባት የኢንዱስትሪ እድገት ለማረጋገጥ ከወትሮው በላይ በቁርጠኝነት እንሰራለን፡፡
Ø በዋና ዋና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የሚታይ የማስፈጸም አቅምና የገንዘብ አቅርቦት ችግር ለመፍታት እንረባረባለን፡፡
Ø በትምህርትና በጤና ዘርፍ የሚታየውን የጥራትና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር በመቅረፍ እየተመዘገበ ያለውን ስኬት አጠናክረን እንቀጥልበታለን፡፡
Ø የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮች በማድረቅና ልማታዊ ሲቪል ሰርቪስ በመፍጠር ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንሰራለን፡፡
Ø በገጠርና በከተሞች የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ግድፈቶች ለመቅረፍ ከህዝቡ ጋር ተቀናጅተን እንሰራለን፡፡
Ø የአጋር ድርጅቶች የማስፈጸም አቅምን ለማጎልበትና የክልላቸውን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት እንዲፈጽሙ ድጋፍ እናደርጋለን ፡፡
Ø የህገ መንግስታችን መርሆዎች የሚጋጩ የአክራሪነት አስተሳሰቦች ከመላው ህዝባችንጋር በመሆን እንታገለዋለን፡፡
Ø ህጋዊና ሰላማዊ መንገድን ተከትለው ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተባብረን እንሰራለን፡፡
Ø የመሪያችን የመለስ ዜናዊ መርሆዎችና አስተምርሆዎች መላው ህዝብ እንዲያውቃቸውና እንዲጠቀምባቸው ለማድረግ በትጋት እንሰራለን፡፡
Comments
Post a Comment