የደ.ኢ.ህ.ዴ.ን. 8ኛ ጉባዔ በሀዋሳ ተጀመረ


የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደ.ኢ.ህ.ዴ.ን./ 8ኛ ጉባዔ መጋቢት 9/2005 ረፋድ ላይ በሀዋሳ ከተማ ተጀመረ፡፡

በጉባዔው መክፈቻ የድርጅቱ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚ/ር ኃይለማርያመ ደሳለኝ  ደ.ኢ.ህ.ዴ.ን. መስመሩን በማጥራትና ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብን በማጉላት የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ ልማት እንድረጋገጥ አድርጓል ብለዋል፡፡


በደቡብ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ለተመዘገበው የኢኮኖሚ እድገት የክልሉ ህዝብ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው አቶ ኃይለማርያም ገልፀዋል፡፡ የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊን መስዋዕትነት ተከትሎ የክልሉ ህዝብ ራዕያቸውን ለማስቀጠል በገባው ቃል መሰረት የህዳሴ ጉዞውን ለማሳካት እየተካሄደ ያለው ጥረት የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡

በደቡብ ክልል የተጀመሩትን የልማት ስራዎች በማጠናከርና ለልማት ሰራዊት ግንባታ ትኩረት በመስጠት በተደራጀ መልኩ ሁለንተናዊ ዕድገት ለማስመዝገብ የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች የአመራርነት ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር አቶ ሽፈራው  ሽጉጤ  በበኩላቸው የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎችን በእልህ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ጥረት በሚደረግበት ወቅት ላይ ጉባዔው የሚካሄድ መሆኑን በመግልጽ በሰላም በድልና በልማት ጎዳና ሆነን  የሚካሄደውን ጉባዔ ውሳኔዎች የክልሉ ህዝብና መንግስት ለማስፈፀም ዝግጁ ናቸው ብለዋል

በጉባዔው ላይ 1200 ታዳሚዎች  በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ የተለያዩ ፓርቲዎች ለደ.ኢ.ህ.ዴ.ን. ያላቸውን አጋርነት በመግለፅ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር