የሃዋሳ ከተማ ሴቶች በምርጫው በንቃት በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን ገለጹ

አዋሳ የካቲት 02/2005 በመጪው ሚያዝያ ወር በሚካሄደው የአካባቢና ከተማ ምክር ቤቶች ምርጫ በንቃት በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ሴቶች ገለጹ፡፡ በከተማው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሴቶች እንደገለጹት ህገ መንግስቱ ያጎናፀፋቸውን የመምረጥና መመረጥ መብት በመጠቀም በሀገሪቱ ለተጀመሩ የልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት እየሰሩ ነው፡፡ ወይዘሮ አምሳሉ ገርጎ፣ ወይዜሮ መሰሉ ደሳለኝ፣ ወይዜሮ ፀሀይ ታፈሰ፣ ወይዜሮ ጌጠ ጉግሳና ወጣት ጥሩነሽ እንድሪያስ ሴቶች ሃብት የማፍራት፣ እኩል ተጠቃሚነት፣የመደራጀትና ሌሎች መብቶቻቸው የተረጋገጠበት ህገ መንግስት ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ የሚያስችል መሪ እንደሚመርጡ ተናግረዋል፡፡ ሴቶች በቀድሞው ስርአቶች ይደረሰባቸው ከነበረው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ መፍትሄ ያገኙት ህገ መንግስቱ ባረጋገጠላቸው መብት በመሆኑ እነዚህን መብቶች ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ምርጫ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ በክልሉ የሚገኙ ሴቶች ከበርካታ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በመላቀቅ በልማትና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ እኩል የመሳተፍ ዕድል ባለቤት የሆኑት በሕገመንግስቱ በመሆኑ ለምርጫው ልዩ ትኩረት ሰጥተው መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=5350&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር