በሴቶች ጥሎ ማለፍ ጨዋታ መከላከያና ሐዋሳ ከነማ ወደ ተከታዩ ዙር አለፉ

የካቲት 19/2005 ዓ.ም በተካሄደው የሴቶች ጥሎ ማለፍ ጨዋታ መከላከያ ከሐዋሳ ከነማ 1 ለ 1 ተለያዩ፡፡


በአዲስ አበባ ስታዲየም የካቲት 19 በተደረገው ጨዋታ ሐዋሳ ከነማ ከሜዳው ውጭ በተለይ ከእረፍት መልስ ጠንካራው መከላከያ ላይ የወሰደው የበላይነት አድናቆት አሰገኝቶለታል፡፡



ሐዋሳ ከነማ በርካታ ግብ ሊሆኑ የሚችሉ አጋጣሚዎችን አምክኗል፡፡

በሁለቱም በኩል የተገኙት ፍጹም ቅጣት ምቶች ወደ ግብ ሳይቀየሩ ቀርተዋል፡፡

በመጀመሪያ ዙር ሐዋሳ ላይ መከላከያ 2 ለ 1 ማሸነፉን ተከትሎ በ3 ለ 2 አጠቃላይ ውጤት ወደ ተከታዩ ዙር አልፏል፡፡

በቀጣዩ መከላከያ የደደቢት ተጋጣሚ እንደሚሆን ለማወቅ ተችሏል፡፡

መብራት ኃይል ከሐረር ቢራ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ደግሞ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል ፡፡
http://www.ertagov.com/ertasport/erta-tv-news-football-addis-ababa-ethiopia/39-amharic-news-catagory-of-sport-football-erta-tv-addis-ababa-ethiopia/1585-2013-02-27-12-17-40.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር