በመካከለኛው የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ አካባቢ የነዳጅ ልማትና ፍለጋ ሊካሂድ ነው


አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ ኦይል ኮርፖሬሽን በመካከለኛው የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ አካባቢ የነዳጅ ልማትና ፍለጋ ሊያካሂድ ነው።
የማዕድን ሚኒስቴርና ኩባንያው በፍለጋው ላይ ዛሬ የስምምነት ሰነድ ተመፈራርመዋል።
በፊርማው ወቅትም የማዕድን ሚኒስትሯ ወይዘሮ ስንቅነሽ እጅጉ ነዳጅ ፈላጊ ኩባንያው በሃገሪቱ ጥናቶችን ሲያደርግ እንደመቆየቱና በሌሎች ሃገራትም ስኬታማ ስራዎችን እንደመስራቱ ፥  ፍለጋው ውጤታማ ይሆናል ብለን እናምናለን ብለዋል።
የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጀምስ ፍሊፕስ ደግሞ በኢትዮዽያም ተስፋ ሰጪ ጥናቶችን አካሂደናል ወጤታማ እንደምንሆነም እምነታችን ነው ብለዋል ።
ከቱሎው ኦይል ጋር በጋራ እያካሄድን ያለው ቁፋሮም በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውጤቱን እናሳውቃለን ብለዋል ።

በእመርታ አስፋው

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር