የክልሉ ምክር ቤት ሶስተኛ ዓመት አራተኛ ዙር ስድስተኛ መደበኛ ጉባኤ በሃዋሳ ከተማ እንደቀጠለ ነው


በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በበጀት አመቱ አጋማሽ በየዘርፉየተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት የተመዘገበባቸው መሆኑን የክልሉ ርዕሰመስተዳድር አስታወቁ 


የክልሉ ምክር ቤት ሶስተኛ ዓመት አራተኛ ዙር ስድስተኛ መደበኛ ጉባኤ በሃዋሳከተማ እየተካሄደ ነዉ ።ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የክልሉን የግማሽበጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት በየስራ ዘርፉ ካለፈዉ ዓመት ክንውን ምርጥ ተሞክሮዎችንበመውሰድና በማስፋት ስትራተጂ በመጠቀም ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል 

በመንግስትና በህብረተሰቡ የተሟላ ተሳትፎ የኪራይ ሰብሳቢነትን ችግሮችን ለመቅረፍ በሚያሰችል መልኩ በገጠርና በከተማ የተለያዩ ተግባራትንበማከናወን ለውጥ ማምጣት የተቻለ መሆኑን አስታዉቀዋል 

ባለፉት ስድስት ወራት በግብርና ልማት፣ በመንገድ ግንባታና በቀበሌ ተደራሽ መንገድ ስራዎች የገጠር ቀበሌዎችን ዕርስ በዕርስና ከዋና መንገድጋር በማገናኘት 705 ኪሎ ሜትር መንገድ ተገንብቶ መጠናቀቁን የገለፁት አቶ ሽፈራው በዚህም አርሶና አርብቶ አደሩ ምርቱን ለገበያ በማቅረብተጠቃሚ መሆኑን አመልክተዋል 

መንገዶቹ በሚገነቡባቸው አካባቢዎችም በማህበር ለተደራጁና በጉልበት ሰራ ለተሰማሩ 106 ሺህ በላይ ሰዎች የስራ ዕድል መፈጠሩንጠቁመው 668 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ለመንገዱ ግንባታ 65 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነጻ የጉልበት አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንገልጸዋል።

የትምህርት ጥራት ፍትሀዊነትና ተደራሽነት በማረጋገጥ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ለማስቻልእንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በሚሰጡ ስልጠናዎች ጥራትና ተፈላጊነት ዙሪያ የታቀዱ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመዋል።

በህዝብ ንቅናቄ የታጀበውን መከላከልን መሰረት ያደረገ የጤና ፕሮግራም አጠናክሮ በማስቀጠል ወባና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን በወረርሽኝመልክ እንዳይከሰቱ መከላከል መቻሉንም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

በክልሉ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን አምና ከነበረበት በገጠር 55 በመቶ ወደ 74 በመቶ ፣በከተማ 88 በመቶ ወደ 94 በመቶበማድረስ አበረታች ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸዉን አቶ ሽፈራው አስታውቀዋል።

በስራ ዕድል ፈጠራ በቀበሌ ተደራሽ መንገድና በኮብል ስቶን መንገድ  በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ፣በአዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታናበተለያዩ ዕድገት ተኮር የስራ ዘርፎች በስድስት ወሩ 69 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ ዕድል መፈጠሩን አቶ ሽፈራዉ በሪፖርታቸውጠቁመዋል።

ምንጭ ኢዜአ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር