በደቡብ ክልል ስድስተኛው የአርሶ አደሮች ቀን በመጪው ሳምንት መጨረሻ ላይ በሀዋሳ ይከበራል

አዋሳ የካቲት 07/2005 ስድስተኛው የአርሶ አደሮችና ከፊል አርሶ አደሮች በዓል በደቡብ ሕዝቦች መስተዳድር በክልል ደረጃ ከየካቲት 16 ቀን እስከ 18/2005 እንደሚከበር የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ። በበዓሉ ላይ በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ አርሶ አደሮችና ባለድርሻ አካላት ይሸለማሉ። በቢሮው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ተወካይ አቶ ሊሬ አቢዩ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ለስድስተኛ ጊዜ በክልሉ በሚከበረው በዓል ላይ 660 አርሶ አደሮች ከፊል አርሶ አደሮች የልማት ባለሙያዎች በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሸለማሉ። ''የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የመለስን የብልፅግና ራዕይ እናሳካለን'' በሚል መሪቃል በሚከበረው የክልሉ አርሶ አደሮች በዓል ተሸላሚ ከሚሆኑ 660 ባለድርሻ አካላት 390ዎቹ አርሶ አደሮች መሆናቸውን ገልፀዋል። ከተሸላሚ አርሶ አደሮች መካከል 117 ከግብርና ተነስተው እሴት በመፍጠር ወደ ባለሀብትነት ደረጃ በማደግ በሌላ መስክ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙባቸው መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም 82 ሴት አርሶ አደሮችና 54 ወጣት አርሶ አደሮች እንዲሁም የእረፍት ጊዜያቸውን ከአርሶ አደሩ ጋር በማሳለፍ በግብርናው መስክ ለተገኘው ውጤት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ 167 የልማት ባለሙያዎች እንደሚገኙበት አስታውቀዋል። በክልል ደረጃ ተሸላሚ ከሚሆኑት መካከል 171 አርሶ አደሮችና ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚከናወነው የአርሶ አደሮች ቀን ላይ ተሸላሚ እንደሚሆኑ አቶ ሊሬ ጠቁመዋል።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=5486&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር