በደቡብ ክልል ከአምስት ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብ በመራጨነት ተመዘገበ

ሃዋሳ ጥር 24/2005 በመጪው ሚያዝያ በሚካሄደው የአከባቢና ከተማ አስተዳደር ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ከአምስት ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብ በመራጭነት ተመዝግቦ ካርድ መውሰዱን በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ሕዝቦች ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገለጸ። በደቡብ ክልል በመራጭነት ተመዝግቦ ካርድ ከወሰደው ህዝብ መካከል ከሁለት ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚበልጡት ሴቶች ናቸው፡፡ ኃላፊው አቶ አብርሃም ጌዴቦ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በሀገር ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ በሚካሄደው የአከባቢና ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ከታህሳስ 21/2005 እስከ ጥር 21/2005 ድረስ ከአምስት ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብ ተመዝግቧል መራጮቹ ምዝገባውን ያደረጉት በክልሉ 14 ዞኖች 4 ልዩ ወረዳና በ22 የከተማ አስተዳደር በተቋቋሙ 8 ሺህ 130 ምርጫ ጣቢያዎች መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ከ40 ሺህ ስድስት መቶ የሚበልጡ ምርጫ አስፈፃሚዎች እየሰሩ መሆኑን አስታውቀው በተመሳሳይ ቁጥር የህዝብ ታዛቢዎች ተመርጠው እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የአከባቢ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አስፈፃሚዎች፣ የሙያ ማህበራት፣ ህብረተሰቡና ሌሎች የባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ምርጫ አስፈፃሚዎች በበኩላቸው ጥር 24 እና 25 በሚካሄደው ልዩ ምዝገባ ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ያልተመዘገቡ መራጮች ተመዝግበው ካርድ በመውሰድ ህገ መንግስታዊ መብታቸውን መጠቀም እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=5093&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር