የ2005 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮና የካቲት 17 ይጀመራል ፤የያዝነውን አመት ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከነማ በ19 ነጥብ ይመራል


በአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ለሳምንታት ተቋርጦ የቆየው የ2005 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመጪው የካቲት 17 እንደሚጀመር ፌዴሬሽኑ አስታወቀ፡፡

በእለቱ ከሚከናወኑት የ10ኛ ሳምንት ግጥሚያዎች መካከል ኢትዮጵያ ቡና ከደደቢት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ የሚያካሂዷቸው ጨዋታዎች ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡


የያዝነውን አመት ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከነማ በ19 ነጥብ ይመራል፡፡ ደደቢት በ18 ነጥብና በ9 ተጨማሪ ግብ ሁለተኛ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በተመሳሳይ ነጥብና በ6 ግብ ክፍያ ሶስተኛ፣ ኢትዮጵያ ቡና በ16 ነጥብ 4ኛ ሆነው ይከተላሉ፡፡


በዘንድሮዉ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ለፍጻሜ ግማሽ የደረሱት ቡድኖች በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮናና ኮንፌዴሬሽን ካፕ የሚሳተፉት ቅዱስ ጊዮርጊስና ደደቢት የመልስ ጨዋታቸውን የካቲት 23 እና 24 አዲስ አበባ ስታዲየም ካከናወኑ በኋላ ለማካሄድ መታቀዱንም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡


በተመሳሳይ የሴቶች ምድብ ጥሎ ማለፍ በመጪው የካቲት 10/2005 ይካሄዳል፡፡


ኢትዮጵያ ቡና ከአርባምንጭ ፣ ደደቢት ከቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አበባ ላይ ይጫወታሉ፡፡ ሙገር ከአዳማ ፣ ሐረር ቢራ ከመብራት ሃይል ፣ ሐዋሳ ከነማ ከመከላከያ በዕለቱ የሚከናወኑ ግጥሚያዎች ናቸው ፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫ በምድብ አንድ ደደቢት በ18 ነጥብ ፣ኢትዮጵያ መድህን 12 ነጥብ፣ በምድብ ሁለት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ16፣ መከላከያ በ11፣ በምስራቅ ምድብ አዳማ ከነማ በ15፣ ድሬደዋ ከነማ በ12፣ በደቡብ ምድብ ሀዋሳ ከነማ በ9 ነጥብና በ6 ተጨማሪ ግብ ሲዳማ ቡና ፣ አንደኛና ሁለተኛ በመሆን ምድቡን በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር