በሀዋሳ ከተማ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመስማራት ከሃገር ውስጥም ሆነ ከውጪ የሚመጡ ባሀብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የከተማው አስተደደር አስታወቀ፡፡

ባለፉት አራት አመታት በከተማው በባለሀብቶች በተከናወኑ የኢንቨስትመንት ስራዎች ከ23ሺህ በላይ ነዋሪዎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡
በሌላም በኩል የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ ባለሃብቶች በአጭር ጊዜ ወደ ስራ እንዲገቡ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል፡፡
የሀዋሳ ከተማ በሃገር አቀፍ ደረጃ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ከተሞች በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀስ ሲሆን ለዚህም እንደምክንያት የሚነሳው ለንግድ እንቅስቃሴ የምትመች መሆኑና የሃይቅዳር ከተማ መሆኗ እንደሆነ ይነገራል፡፡
ከተማዋን የቱሪስት መዳረሻ፣ የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ በተያዘው አመት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍ ገልፀዋል፡፡
በተለይ ይህን ስራ የበለጠ ማስኬድ እንዲቻል ከተማውን የማስተዋወቅ ስራ ትኩረት እንደተሰጠው አመልክተዋል፡፡
4ኛው የከተሞች ሳምንት ተካሂዶ  ሃዋሳ ሁለት ዋንጫ በማግኘት አሸንፋ ከተመለሰች በሁዋላ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት ከሃገር ውስጥም ሆነ ከውጭ በርካታ ባለሃብቶች ጥያቄ እያቀረቡ እንዳለ አቶ ዮናስ ገልፀዋል፡፡
በዚህም የከተማ አስተዳደሩ የተሻሉ አሰራሮችን በመዘርጋት ባለሀብቶችን ለማስተናገድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ ባለፋት አራት አመታት ውስጥ ኢንቨስት ባደረጉ ባለሃብቶች ከ 23 ሺህ በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውንና ኢንቨስትመንት ይበልጥ በከተማዋ ለማስፋፋት ዘመናዊ ድረ ገጽ በመክፈት የማስተዋወቅ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል በተለያዩ ወቅቶች የኢንቨስትመንት ቦታ ወስደው ያላለሙ ባለሃብቶች እንዳሉ አረጋግጠናል ያሉት አቶ ዮናስ፣ 60 ባለሀብቶችን አሰተዳደሩ ወደ ልማት እንዲገቡ ማወያየቱንና ከስምምነት ላይ መደረሱን አስረድተዋል፡፡
በከተማው የሚካሄዱ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ከተማው ውበትም ሆነ እድገት እንዲሁም ለነዋሪው የስራ እድልን ከመፍጠር አኳያ ያለው ፋይዳ የጐላ በመሆኑ ባለሃብቶች በፍጥነት ወደ ስራም እንዲገቡ በዚህ አጋጣሚ ከንቲባው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/08TahTextN205.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር