የሕወሓት አብዮት ሰለባዎች.. የአዋሳ ከንቲባ አቶ ሽብቁ እስር ተፈረደባቸው


የሕወሓት አብዮት ሰለባዎች.. የአዋሳ ከንቲባ እስር ተፈረደባቸው 
 ከሰሞኑ በደቡብ ክልል ጉራ ፈረዳ ወረዳ የአማራ ክልል ተወላጆች ተባረው መሬታቸው ለሌሎች የስርዓቱ ደጋፊዎችና አባላት በሃራጅ መሸጡን ዘ-ሐበሻ ስትዘግብ ቆይታ ነበር። ከአዲስ አበባ የመንግስት ሚዲያዎች ያስተላለፉት ዜና ደግሞ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪ ላልሆኑ ሰዎች መሬት የሸጡ የክልሉ ባለስልጣናት በሙስና ወንጀል ተከሰው እንደተፈረደባቸው ያትታሉ። የሕወሓት/ኢሕአዴግ ሥር ዓት አብዮት ለስልጣኑ ታማኝ ያልሆኑትን በሙስና ሰብብ ሲበላ መቆየቱን ያስታወሱት አስተያየት ሰጪዎች በታምራት ላይኔ ጀምሮ በስዬ አብርሃ ለጥቆ አሁን የጸረ ሙስና ሕጉ የቂም በቀል መወጣጫ ሆኗል ሲሉ ይተቻሉ።
ኃላፊ በነበሩበት ወቅት ስልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም መሬት ለግለሰቦችና ድርጅቶች ሰጥተዋል በሚል የሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩ የቀድሞ የሃዋሳ ከተማ ከንቲባና ሌሎች ስድስት ተከሳሾች በእስራትና በገንዘብ መቀጣታቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እያዳነቁ ዘግበዋል። በማዳነቂያ ዜናቸው ላይ “ግለሰቦቹ ለመኖሪያ ቤት የማይፈቀድን ቦታ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፥ የተጻፈውን ዕገዳ በመጣስ የተለያዩ ግለሰቦች እና ጋዜጠኞችን ጨምሮ በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ላልሆኑ ስምንት ሰዎች መሬትበመስጠታቸው ነው የተከሰሱት (የተሰመረበትን ይመልከቱ)ሲሉ ነው የመንግስት ሚድያዎች የዘገቡት።
እነዚሁ ሚዲያዎች ዘገባቸውን ሲያጥናቅር “የደቡብ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የነበሩትን ፥ አቶ ሽብቁ ማጋኔን ጨምሮ 6 ተከሳሾች ላይ ከአንድ እስከ ስምንት ዓመት በሚደርስ እስራትና ከ2 እስከ 20 ሺህ ብር እንዲቀጡ፤ ፍርድ ቤቱ የክልሉ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ይግባኝ በጠየቀባቸው ፥ አቶ ሽብቁ ማጋኔ፣ አቶ እንድርያስ ፉላሳ፣ አቶ ጸጋዬ አረጋ፣ አቶ ጉደታ ጉምቤ፣ አቶ አስራት ግቻሞና አቶ ከበደ ካያሞ ላይ የእስራትና ገንዘብ ቅጣቱን የወሰነው የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ በመሻር ነው።” ብለዋል። የመንግስት ሚዲያዎቹ “በዚሁ መሰረት በአቶ ሽብቁ ማጋኔ ላይ የአምስት አመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራትና በአምስት ሺህ ብር ፣ አቶ እንድሪያስ ፉላሳና ፥ አቶ ጉደታ ጉምቤ እያንዳንዳቸው በ5 ዓመት ከ6 ወር እስራትና በ15 ሺህ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። አቶ አስራት ግቻሞ አንድ አመት ከ2 ወር እስራትና የ2 ሺህ ብር መቀጫ ፣ እንዲሁም አቶ ከበደ ካያሞ በአንድ ዓመት እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ጉዳያቸው በሌሉበት የታየው አቶ አረጋ ጸጋዬ በስምንት ዓመት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል ።” ሲሉ ዘገባቸውን አጠናቀዋል።
የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች “በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ላልሆኑ ስምንት ሰዎች መሬት ሰጣችሁ” ተብለው በተፈረደባቸው የሕወሓት አብዮት ሰለባዎች ዙሪያ ምን ትሉ ይሆን? የስልጣን ላይ እንቅልፍ ያሉትስ ነገ በኔ ላይ አይመጣም ብለው ቁጭ ያሉትስ ምን ይሉ ይሆን? አስተያየታችሁን አስቀምጡ።
http://minilik-salsawi.blogspot.com/2012/12/blog-post_9722.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር