ከተለያዩ የገቢ አርዕሰቶች ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን በሲዳማ ዞን የአለታ ጩኮ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡


የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መንግስቱ መለስ እንደገለፁት የተገኘው ገቢ በዓመት ውስጥ ሊሰበሰብ ከታቀደው የ3ዐ ሚሊዮን ብር አካል ክንውኑም 1ዐ7 ብልጫ እንደሚኖረው አስታውቋል፡፡
ገቢው ከአመና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ1 ሚሊዮን ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

የመስሪያ ቤቱ ሠራተኞችን በገቢ አሰባሰብ ስምሪት በ24 ሰዓት በፈረቃ በማድረግና ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ መስመር ማስገባት መቻሉ አቶ መንግስቱ ተናግረዋል፡፡
ለገቢው መጨመር አስተዋፅኦ እንደነበረው በወረዳው የግብር ከፋይና ምዝገባ ክትትል የንግዱ ማህበረሰብ ግብር በወቅቱ በመክፈል ሀላፊነቱን እንዲወጣ ትልቅ አገዛ እንዳደረገላቸው ገልፀዋል፡፡
አንዳንድ  ግብር ከፋዮች በሰጡት አስተያየት መንግስት ያቀዳቸውን ውጥኖች ማሳካት ግብርን በወቅቱ መክፈል የገባነው ቃል እንወጣለን ሲሉ መናገራቸውን የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር