የቡና ምርት መጠንና ጥራትን በማስጠበቅ በአለም ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ በሀዋሳ ከተማ በተዘጋጀው የባለ ድርሻ አካላት ግብረ ኃይል ፎረም ስብሰባ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንዳሉት የቡና ግብይት ስርዓቱ ውጤታማ በማድረግ የአርሶ አደሩን ገቢና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡

ባለፉት ተከታታይ የምርት ዘመናት በተደረገ ሰፊ እንቅስቃሴ በቡና ምርት ዝግጅት ስራ ላይ የነበሩ ድክመቶችን ለይቶ በማስወገድ ረገድ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋልም ብለዋል፡፡
ዘመናዊ የግብይት ስርዓቱን ጤናማ በማድረግ ሀገሪቷ ከዘርፉ የምታገኘው የገቢ እቅድ ለማሳካት ምርቱን በወቅቱ ያለማቅረብና ህገወጥ የቡና ግብይቶች የመሳሰሉ ችግሮች ለማስወገድ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው እንዲንቀሳቀሱም አሳስበዋል፡፡
የቡና ግብይ ማዕከላትን በማጠናከር የቡና ጥራትና ንግድ ቁጥጥሩ በአስተባባሪ ግብረ ኃይሎች ሊጠናከር ይገባልም ብለዋል፡፡
የንግድ ሚኒስቴር ማኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ እንዳሉተም የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተነድፎ ተግባራዊ መሆን ከተጀመረ ወዲህ ሀገሪቷ ከውጭ ምርቶች የሚገኘው ገቢ እያደገ መጥቷል፡፡
በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መጨረሻ ሀገሪቷ ከውጭ ምርቷ የምታገኘው ገቢ 1ዐ ነጥብ አራት ቢሉዮን ዶላር ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ያሉት ሚኒስትሩ በያዝነው ዐመት 5 ቢልዮን ዶላር ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የቡ ምርቱ መጠንና ጥራት በማሻሻልም ዘንድሮ ከአንድ ነጥብ አነድ ቢልዮን ዶላር በላይ ገቡ እንዲገኝ የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካት ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መንቀሳቀስ አለባቸው ብለዋል፡፡
ከአምራቾች እስከ ገበያ ድረስ ያለው የጥራትና የአቅርቦት ችግሮች በማስወገድ በያዝነው የምርት ዘመን 3መቶ 43 ሺህ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም አሳስበዋል፡፡

በውይይቱ የቡና ምርት መጠንና ጥራት እንዲሁም የግብይት ስርዓቱ እየተሻሻለ ቢመጣም ወደፊት የተሻለ ዋጋ ሊያወጣ ይችላል በሚል ቡናን አከማችቶ ያለመሸጥ ችግር፣ ህገወጥ ግብይት ሙሉ በሙሉ አለመወገድ፣ የመጀመሪያ የቡና ግብይት ማዕከላት አለመጠናከርና፣ የብድር አቅርቦት ችግሮች በውስንነት ተጠቅሰዋል፡፡
ህገወጥ  የቡና ዝውር፣የቡና ጥራት ቁጥጥና ግብይት ግብረ ሀይል አለመጠናከር እንዲሁም እንደ ጉራጌ ዳውሮ ዞኖችና ኮንታ ልዩ ወረዳ የመሳሰሉ ቡና ቢያመርቱም ለማዕከላዊ ገበያ ያለማቅረባቸውም መጠነኛ ችግሮች እንደሆኑ ተመልክተዋል፡፡
ባለድርሻ አካላት ችግሮችን ተቀናጅተው በማስወገድ አቅራቢዎች በመጋዘናቸው ያለውን ቡና ሙሉ በሙሉ እስከ ታህሳስ ወር ለገበያ ማቅረብ እንዳለባቸውና የሀገሪቷ የቡና ምርት ከሌሎች ቡና አቅራቢ ሀገራት ተወዳድሮ የተሻለ ዋጋ እንዲኖረው በምርት ዘመኑ እስከ የካቲት ወር ድረስ ለመሸጥ ተስማምተዋል፡፡
የጥራትና የግብይት ስርዓቱን በማክበርና በማስከበር የአርሶ አደሩ ብሎም የሀገሪቷ ጥቅም ለማስጠበቅ እንደሚጥሩም ተሳታፊዎቹ አረጋግጠዋል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/10HidTextN405.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር