በተያዘው የበጀት አመት በሽታን በመከላከልና ጤናን በማጎልበት የህክምና አገልግሎቶችን በጥራትና በፍትሀዊነት ለህብረተሰቡ ለማዳረስ አቅዶ እየሰራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የጎርቼ ወረዳ ጤና አጠባበቅ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የወረዳው ጤና አጠባበቅ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተረፈ ያዕቆብ እንደገለፁት በወረዳው በጤናው ዘርፍ የሚሰጡትን አገልግሎቶች ተደራሽነት ለማረጋገጥ የጤና አገልግሎት ተቋማትን በየቀበሌው በማስፋፋትና የጤና ልማት ሠራዊትን በመገንባት በተያዘው የበጀት ዓመት በዘርፉ ሰፊ ስራ ለመስራት ታቅዷል፡፡

በወረዳው ባለፈው የበጀት ዓመት የእናቶችንና የህፃናትን ጤና በመንከባከብ ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር እንዲያስችል የፀረ ዘጠኝና የፖሊዬ ክትባቶች ተደራሽነት በበቂ ሁኔታ መከናወኑን ኃላፊው ገልፀው ከዚህም የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር በዘንድሮው ዓመትም የተሻለ አፈፃፀም ይመዘገባል ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በወረዳው የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ አደረጃጀቶችንና ከ5መቶ 30 በላይ ቁርኝቶችን በመጠቀም አስራ ስድስቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፖኬጆችን ለመተግበር በ6 የጤና አጠባበቅ ጣቢያዎችና በ21 ጤና ኬላዎች ህብረተሰብ አቀፍ የጤና ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙም ገልፀዋል፡፡ አምባዬ አዳነ ከበንሳ ቅርንጫፍ እንደዘገበው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/6TikTextN305.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር