በሲዳማ ዞን የአማራጭ ኢነርጂ ልማት በመጠናከር ላይ ነው
ሰሞኑን
በሃዋሳ ከተማ በተካሄደው የደቡብ ክልል የውሃ
ጉባኤ የቀረበው የ2004
ኣ/ም
የመምሪያው የስራ ኣፈጻጸም የተመለከተው
ኣንድሪፖርት እንዳመለከተው በዞኑ ውስጥ
በኣማራጭ ኢነርጂ ልማት ዘርፍ ኣበራታች ስራዎች
ተከናውነዋል።
መምሪያው
በባጀት ኣመቱ ለማከናወን ካቀዳቸው 19
አዲስ
ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አምራቾች ማህበራት እንዲቋቋሙ
በማድረግ ለ3-
ማህበራት
ፕሬስና ሞልድ ተገዝቶ ድጋፍ ማድረጉ
የተገለጸ ሲሆን፤ በ19
ወረዳዎች
በ38
አማካይ
ቦታዎች የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ላይ ለሕብረተሰቡ
ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት ከእቅዱ
በላይ በመስራት 4500
የተሻሻሉ
ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎ አንዲሰራጩ በማድረግ በርካታ የዞኑን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ኣድርጓል፡፡
ከዚህም
በተጨማሪ በሁሉም ወረዳዎች 100
የሚሆኑ
የቤተሰብ የሶላር ተጠቃሚ ማህበራት መደራጀታቸው
ሲገለጽ፤ የኃይል አማራጭ ኢነርጂ አጠቃቀም
ላይ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።
እንደሪፖርቱ
ከሆነ የሶላር
ኢነርጂ ተከላ እና
የባዮ
ጋዝ ግንባታ በተለያዩ
ወረዳዎች የተካሄደ ሲሆን፤ ኣራት የአማራጭ
ኢነርጂ ዳሰሳ ጥናትም
ተከናውነዋል።
Comments
Post a Comment