ዋልያዎቹ ቃል የተገባላቸውን ማበረታቻ ነገ ይቀበላሉ



አዲስ አበባ፣ጥቅምት 5 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋልያዎቹ ቃል የተገባላቸውን የማበረታቻ ሽልማት ነገ በኤድናሞል ህንጻ በሚከናወን ስነ ስርአት ይቀበላሉ። 
የኢትዮጽያ ብሄራዊ ቡድን ለ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሚያልፍ ከሆነ የተለያዩ ድርጀቶችና ግለሰቦች የማበረታቻ ሽልማት እንደሚሰጡ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። ከነዚህ መሀልም የኤድናሞል ባለቤት አቶ ተክለብርሀን አምባዬ ፥ የብሄራዊ ቡድኑ የልምምድ ሜዳ በመገኘት ለእያንዳንዱ ተጫዋች ለመስጠት ቃል የገቡትን ፥ የ25 ሺህ ብር ሽልማት ነገ ከ5 ሰአት ጀምሮ በኤድናሞል በሚከናወነው ስነ ስርአት ያበረክታሉ። 
በነገው እለት በሚከናወነው በዚህ የማበረታቻ ፕሮግራም ከገንዘብ ሽልማቱ በተጨማሪ ፥ ለቡድኑ አባላት በሙሉ የምሳ ግብዣ እንደሚደረግላቸው ባልደረባቸን አራያት ራያ ዘግባለች። 
ድሉን ተከትሎ የሚድሮክ ባለቤት ሼክ ሙሀመድ አሊ አላሙዲ ለብሄራዊ ቡድኑ በአጠቃላይ የአምስት ሚሊየን ብር የማበረታቻ ሽልማት እንደሚሰጡ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር