አመራሮቹ በባለ ዘጠኝ ነጥብ በገለጹት የአቋም መግለጫቸው የሀዋሳን ከተማ የአመራር ስምሪት ከኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳና ብቁ አመራር ከየትኛውም መዋቅር ቢመደብ ትግሉን ለማስቀጠል ቃል ገብተዋል፡፡

ባለፈው አመት ነሐሴ ወር ላይ ነበር በሀዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን በአንዳንድ ወረዳዎች ሁከት የመፍጠር አዝማሚያ የተከሰተው፡፡

የሲዳማ ህዝብ ጥያቄና ፍላጎት ነው በሚል የብሔሩን አቋምና ሀሳብ የማይወክሉ ግን ደግሞ ይህንኑ መንፈስ የያዙ ሁከት የመፍጠር አዝማሚያ መከሰቱ ይታወሳል፡፡

እናም የተፈጠረውን ሁኔታ ለመገምገምና ጉዳዩን ለማጣራት የብሔሩ ተወላጆች የሆኑ ከፌደራል እስከ ወረዳ ድረስ የሚገኙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የተገኙበት ግምገማ ለአንድ ሳምንት ተካሂዷል፡፡

በግምገማው ማጠቃለያ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ሽፈራው ሹጉጤ እንዳሉት የተፈጠሩት ሁኔታዎች የኪራይ ሰብሳቢና የጸረ ሰላም ኃይሎች አጀንዳ እንጂ የሲዳማ ህዝብ ፍላጎት ያለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

በወቅቱ የተፈጠረው ሁኔታ ለማርገብ የተደረገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የኪራይ ሰብሳቢ እና የጸረ ሰላም ኃይሎች የህብረተሰቡን አቅጣጫ ለማስቀየር ያደረጉት ጥረት ያለመሳካቱንና ህልማቸው ቢሳካ ኖሮ በውስጠ ድርጅቱ ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ የከፋ ይሆን ነበር ብለዋል፡፡

የሲዳማ ህዝብ ከየትኛውም ብሔር እና ብሔረሰብ ጋር ተፋቅሮ እና ተከባብሮ የኖረ ወደፊትም የሚኖር ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ ይሁንና ኪራይ ሰብሳቢዎች እና የጸረ ሰላም ኃይሎች በወቅቱ የፈጠሩት አጀንዳ ይህንን ህብረ ብሄራዊነት ለማጥፋት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ በታየባቸው አንዳንድ አመራሮች ላይም በየደረጃው በተካሄደው የሂስ ግለሂስ መድረኮች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱንም የገለጹት ርዕሰ መስተዳደሩ በቀጣይም የኪራይ ሰብሳቢነትን አስተሳሰብ ከምንጩ የማድረቁ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

አመራሮቹ መንታ መንገድ የለም በሚል ርዕስ ለአንድ ሳምንት ያካሄዱትን ግምገማ ያጠናቀቁት በጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም በግለጫ በማውጣት ነበር፡፡

በመሆኑም በየጊዜው የሚፈጠሩ የጥገኘነት እና የጸረ ሰላም ኃይሎች የማደነጋገሪያ አጀንዳ የማይበገር አብዮታዊ ስብዕና የተላበሰ የህዝበ መሪነት ሚናችንን እንወጣለን ብለዋል አመራሮቹ፡፡

አመራሮቹ በባለ ዘጠኝ ነጥብ በገለጹት የአቋም መግለጫቸው የሀዋሳን ከተማ የአመራር ስምሪት ከኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳና ብቁ አመራር ከየትኛውም መዋቅር ቢመደብ ትግሉን ለማስቀጠል ቃል ገብተዋል፡፡

ለዘመናት ተከባብሮና ተዋዶ የኖረውን የሲዳማንና የወላይታን ህዝብ ለማጋጨት ብሎም ለማለያየት ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ጥገኞችና ጸረ ሰላም ኃይሎች የሲዳማን ህዝብ አይወክሉም የሚሉት አመራሮቹም በአቋም መግለጫቸው ካሰፈሩት ውስጥ ይጠቀሳል፡፡

የወጣቱ ዋነኛ ችግር የስራ አጥነት ችግር ነው ያሉት አመራሮቹ ይህን ችግር በገጠር እና በከተማ የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከምን ጊዜውም በላይ መዘጋጀታቸውንም አስታውቀዋል፡፡
ለአንድ ሳምንት በተካሄደው ግምገማ የፌደራል የክልል የዞን የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ እና መካከለኛ የሲዳማ ብሔር ተወላጆች ተገኝተዋል





http://www.smm.gov.et/

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር