የስኳር ምርትን ወደ ውጭ ለመላክ ከፍተኛ ጥረት እንደሚደረግ ተገለጸ



አዲስ አበባ፣ጥቅምት 21 ፣2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የስኳር ምርትን ባለፈው ዓመት ወደ ውጭ መላክ ይጀመራል ተብሎ የነበረ ቢሆንም የስኳር ፕሮጀክቶቹ በታሰበላቸው ፍጥነት እየሄዱ እንዳልሆነ ተገለጸ። 
የስኳር ኮርፖሬሽን እንደሚለው ለፕሮጀክቶቹ መጓተት ዋነኛው ምክንያት የአቅም ውስንነት ነው። 
ቀደምሲልየማስፋፊያስራእየተሳራባቸውየነበሩየስኳርፋብሪካዎችንና ነባርየስኳርፋብሪካዎችንበመጠቀምካለፈውዓመትጀምሮየስኳርምርትለውጭገበያለማቅረብታቅዶየነበረሲሆን፥እንደታቀደውግንማድረግአተቻለም።
የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ልዩ አማካሪ አቶ አስፋው ዲንጋሞ እንዳሉት ፥ የኮንትራክተሮችም ሆነ የአማካሪዎች አቅም ውስንነት ፣ የገንዘብ እጥረት ፣ በበቂ የሰው ኃይል አለመደራጀት ፣ ለፕሮጀክቶቹ መጓተት በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው።

ከፕሮጀክቶቹ ግዝፈትና ውስብስብነት ጋር በተያያዘም ፥ የስኳር ኮርፖሬሽንም ቢሆን የፕሮጀክት አመራርና አስተዳደር ድክመት እንደነበረበትና፥ በአሁን ወቅት ግን ችግሮቹ በመለየታቸው በያዝነው ዓመት ፕሮጀክቶቹን በአዲስ መልክ ለማፋጠንና ለማጠናቀቅ ርብርብ በመደረግ ላይ መሆኑንም ነው ያስረዱት።

ኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶቹን በአዲስ መልክ ለመምራት እንዲያስችለውም ፥ ባለፉት ሶስስት ወራት ቁልፍ ችግሬ ነበር ላለው የአቅም ውስንነት ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል ፥ እየሰራም ነው። የሰው ኃይሉን አቅም ለማጎልበትም በውጭ ሃገራት ጭምር በመላክ የተለያዩ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እያደረገ ነው።

የከሰም ስኳር ፋብሪካ በጣም ከዘገዩት ውስጥ አንዱ ሲሆን ፥ የፋብሪካ ግንባታውንም በዚህ ዓመት በአብዛኛው በማጠናቀቅ በቀጣዩ ዓመት ወደ ማምረት ስራ እንዲገባ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ፥ የወልቃይት፣የበለስና ስድስት ፋብሪካዎች የሚገነቡበት የደቡብ ኦሞ ኩራዝ ፕሮጀክቶችም ላይ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩባቸው ይገኛሉ።

በነዚህ ፕሮጀክቶች ከጥናትና ዲዛይን ስራ ጀምሮ የመስኖ መሰረተ ልማት ፣ የመንገድና የቤቶች ግንባታ ፣ የመሬት ዝግጅትና የአገዳ ተከላ እንዲሁም የፋብሪካ ተከላ ስራ በተለያየ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

አቶ አስፋው እንዳሉት ፋብሪካዎቹ በዚህ ዓመትና በቀጣዩ ዓመት ግንባታቸውን በማፋጠን 2007 ላይ የማምረት ስራ እንዲጀምሩ ከፍተኛ ርብርብ በመደረግ ላይ ነው ፥ ባለፈው ዓመት ለተጠቃሚዎች ከተሰራጨው ከ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል ውስጥ 2 ሚሊየን ኩንታል የሚጠጋው ከውጭ የገባ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ ድረስ ይህ መጠን እየቀነሰ ሄዶ እንደውም በቀጣዩ ዓመት ለውጭ ገበያ ማቅረብ ይጀመራል ፥ ባልደረባችን በዛብህ ማሞ እንደዘገበው።
http://www.fanabc.com/Story.aspx?ID=26640&K=

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር