ደኢህዴን የሲዳማን ህዝብ ፍላጎት እና ጥቅም ካላስጠበቀ ለሲዳማ ህዝብ ምኑ ነው?




(የሲዳማ ተወካዮች እነማናቸው?)
ካለፈው የቀጠለ
ለመሆኑ በተለይ በዚህ ሳምንት ያወጡት የኣቋም መግለጫም ሆነ ወሳኔዎቹ በርግጥ የሲዳማን ህዝብ ይጠቅማሉ? ወይስ የሲዳማን ህዝብ ጥቅም ባያስጠብቁም የደኢህዴን ፖሊስ ለማስፈጸም ያህል የተወሰዱ እርምጃዎች ናቸው?
ይህ የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማ ተወላጆች ለመንጠቅ ታስቦ የተዘጋጀው ጽሁፍ ሆነ እቅድ በቀላሉ ልሳካ እንደማይችል ኣዛጋጆቹ ጠንቅቀው ስለምያውቁ ነበረ ሃሳቡን ለውይይት ኣዘጋጅተውት የነበሩት።


ብዙዎቻችን እንደምናውቀው ደኢህዴን የዛሬ ሶስት ወራት በፊት የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር በጋር ለማስተዳደር በምል ያዘጋጀው የውይይት ጽሁፍ ከሰፊው የሲዳማ ህዝብ እጅ ቀድሞ ገብቶ ለእቅዳቸው ኣለመሳካት ለጊዜውም ብሆን ሳንካ ሆኗል። በጊዜው የክልል ባለስልጣናት ስለ የውይይት ጽሁፉ የተለያዩ መግለጫዎችን መስጠታቸው የምታወቅ ሲሆን በደቡብ መገናኛ ብዙሃን ቀርበው የበሬ ወለደ ወሬ ነው በማለት ህዝብ ለመዋሸት መሞከራቸው እንዲሁ የምታወስ ነው።

በወቅቱም ብሆን ኣንዳንድ ውስጥ ኣዋቂ ምንጮ እንዳሉት የክልሉ ባለስልጣናት በሬ ወለደ ወሬ ነው በማለት ያስወሩት የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር የመበረዝ ኣካሄድ ድርጅቱ ጊዜ ወስዶ ተዘጋጅቶበት መክሮ እና ዘክሮ ያዘጋጀው የውይይት ጽሁፍ መሆኑን ነበር። ይህ የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማ ተወላጆች ለመንጠቅ ታስቦ የተዘጋጀው ጽሁፍ ሆነ እቅድ በቀላሉ ልሳካ እንደማይችል ኣዛጋጆቹ ጠንቅቀው ስለምያውቁ ነበረ ሃሳቡን ለውይይት ኣዘጋጅተውት የነበሩት። ታዲያ ያን ጊዜ የሲዳማ ህዝብ ባሳየው ህዝባዊ ንቅናቄ ተደናግጠው ሀሳቡን ለማድበስበስ ጥረት ኣድርገው ህዝቡን በማረጋጋቱ ረገድ ተሳክቶላቸው ማለት ይቻላል።

ነገር ግን የወቅቱ የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄ ለደኢህዴን ኣመራሮች ኣንድ ትምህርት የሰጣቸው ሲሆን ይህን መሰል በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ሰንሴቲቪ የሆነ ጉዳይ እንዲሳካላቸው ካሰፈለገ ጉዳዩን በቀጥታ ከህዝብ ጋር መክሮ ና ዘክሮ ከመወሰን ይልቅ የራሳቸውን ኣመራሮችን ሰብስቦ እንድወሰኑ በማድረግ ካዛም ውሳኔ የተሰጠበትን ጉዳይ ወደ ህዝቡ ማውረድ እንደ ብቸኛ ኣማራጭ እንድወስዱ ኣድርጓል። ይህም ታላቅ ስህተት እንዲፈጽሙ ኣድርጓቸዋል። ስለዚህም ኣሁን ጊዚያቸውን ጠብቀው ኣካሄዳቸውን ቀይረው በራሳቸው መወሰን የማይችሉትን የሲዳማ ኣመራሮችን ስብስበው ያለ ህዝቡ ፍቃድና ፈላጎት በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ ሌሎች ብሄሮችን ለመቀላቀል ወስነዋል። በአቋም መግለጫቸውም የሀዋሳን ከተማ የአመራር ስምሪት ከኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳና ብቁ አመራር ከየትኛውም መዋቅር ቢመደብ ትግሉን ለማስቀጠል ቃል ገብተዋል፡፡

ከላይ ከኣዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚወርድላቸውን ጸረ ሲዳማ ኣጀንዳ ነው እያስፈጸሙ እንጂ ያሉት ከመቼ ወዲህ ነው በራሳቸው ኣጀንዳ ኖሯቸው ለኣጀንዳቸው መተግበር ሰርተው የምያውቁት?

ደኢህዴን እንደሞኝ ተረት እየደጋገመ የሃዋሳን ከተማ ከሲዳማ ኣስተዳደር ለመንጠቅ የምዶልተው ጉዳይ የሲዳማ ህዝብ በመንገሽገሹ የተነሳ የሃዋሳ ከተማ ጉዳይ ብሎም ደኢህዴን በሲዳማ ህዝብ ላይ የምፋጽመው ደባ ለኣንደና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንድያገኝ በምል የራሰ የሆነ የክልል ኣስተዳደር ይገባኛል ጥያቄ ኣንግቦ ያደረገውን ከዳር እስከ ዳር ያናወጠ ህዝባዊ ንቅናቄ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ሳይሆን የጸረ ሰላም ኃይሎች ጥያቄ ነው በማለት ሰፊውን የሲዳማ ህዝብ ጸረ ሰላም ኃይል በማለት የክልሉ ባለስልጣናት ተሳልቀዋል።

የድፍረታቸው ድፍረት እንደፈለጉ በሚያዙት ሚዲያ ቀርበው የሲዳማ የክልል ጥያቄውን ያነሱት ግለሰቦች ናቸው እነርሱም ብሆኑ የኪራይ ሰብሳቢ እና የጸረ ሰላም ኃይሎች የህብረተሰቡን አቅጣጫ ለማስቀየር ያደረጉት ጥረት ያለመሳካቱንና ህልማቸው ቢሳካ ኖሮ በውስጠ ድርጅቱ ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ የከፋ ይሆን ነበር ብለዋል፡፡ እዚህ ላይ ደኢህዴን የምባለው የጥቅት የሲዳማ ኣመራሮች ድርጅት እንጅ ለሲዳማ ህዝብ የቆሞ ድርጅት ኣለመሆኑን የረሱት ይመስላል።

የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ በታየባቸው አንዳንድ አመራሮች ላይም በየደረጃው በተካሄደው የሂስ ግለሂስ መድረኮች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱንም የገለጹት ርዕሰ መስተዳደሩ በቀጣይም የኪራይ ሰብሳቢነትን አስተሳሰብ ከምንጩ የማድረቁ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡እዚህ ላይ ሌላው የረሱት እና ልያውቁት የምገባው ነገር ኣብሯቸው ያሉት ኣመራሮች ቢሆኑ ለሆዳቸው ብለው እንጂ በነጻ ኣዕምሮኣቸው ማሰብ የምችሉ መሆናቸውን ነው። በራሳቸው የምያስቡትንም እና ለሲዳማ ህዝብ ጥቅም መከበር የታገሉ የደኢህዴን ኣመራሮችም ቢሆን በክራይ ስብሳቢነት ልኮነኑ እንደማይገባ ብሎም ዋነኛ ኪራይ ሰብሳቢዎች ጸረ ሲዳማ የሆነት በውሳኔው ላይ የተሳተፉት የሲዳማ ኣመራር ተብዬዎች መሆናቸውን ነው።

በመሆኑም በየጊዜው የሚፈጠሩ የጥገኘነት እና የጸረ ሰላም ኃይሎች የማደነጋገሪያ አጀንዳ የማይበገር አብዮታዊ ስብዕና የተላበሰ የህዝበ መሪነት ሚናችንን እንወጣለን ብለዋል የምሉት ማንን ለማለት እንደፈለጉ ለራሳቸውም ቢሆን ግልጸ የሆነላቸው ኣይመስልም፡፡ ምክንያቱም እነዚሁ ኣመራሮች የጸረ ሲዳማ ኃይሎች ጥገኛ ኣመለካከት ኣራማጆች ናቸውና። ከላይ ከኣዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚወርድላቸውን ጸረ ሲዳማ ኣጀንዳ ነው እያስፈጸሙ እንጂ ያሉት ከመቼ ወዲህ ነው በራሳቸው ኣጀንዳ ኖሯቸው ለኣጀንዳቸው መተግበር ሰርተው የምያውቁት?
ለመሆኑ ይህ መግለጫ የወላይታው ሰውዬ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆኑን ተከትሎ ወደ ወላይታዎቹ ጠጋ በማለት ኣንጄታቸውን ለመብላት ተፈልጎ ይሁን የምል ጥያቄም ጭሮብኛል።



በኣቋም መግለጫው ላይ ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል ሌላው እኔን በተለይ የገረመኝ ጉዳይ የሲዳማ ህዝብ ከሌላቸው ህዝብ ጋር ያለውን ተፋቅሮ የመኖር ባህል በተመለከተ ያነሱት ነጥብ ነው። የሲዳማ ህዝብ ከየትኛውም ብሔር እና ብሔረሰብ ጋር ተፋቅሮ እና ተከባብሮ የኖረ ወደፊትም የሚኖር ስለመሆኑ የእነርሱን ምስክርነት ኣያሻውም ነገር ግን ለዘመናት ተከባብሮና ተዋዶ የኖረውን የሲዳማንና የወላይታን ህዝብ ለማጋጨት ብሎም ለማለያየት ሲንቀሳቀሱ... በማለት በኣቋም መግለጫቸው ያነሷት ነጥብ ወዴት ወዴት እንድል ኣስብሎኛል። ምክንያቱም በሲዳማ እና ወላይታ ህዝቦች መካከል የተለየ ግጭት የለም ኖሮም ኣያውቅም፤ ባይሆን ሆኖም ግጭት እንዳለ ኣስመስለው መግለጨ ስጥተዋል።

ከላይ እንዳነሳሁት የሰሞኑ ውሳኔው የሲዳማን ህዝብ ልጠቅም የምችልበት ሁኔታ ምን እንደሆነ በግልጽ እነኝሁ የሲዳማ ኣመራሮች መግለጽ ኣልቻሉም። እንዳውም ከግል ጥቅም ኣንጻር ካልሆነ በስተቀር የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር የሲዳማ ህዝብ በመንጠቅ ለሌላው መስጠት እንዴት ሲዳማን ልጠቅም እንደምችል ለማብራራት እነሱም ብሆኑ ትንሽም ብሆን ረቀቅ ያለ ኣእምሮ ሳያስፈልጋቸው ኣይቀርም፤ በኣጠቃላይ የፍቅር ከተማዋን መነጠቅ ለሲዳማ እንዴት ነው የምጠቅመው? የራሱን ለሌላው ኣሳልፎ እየሰጠ እንዴት ነው ተጠቃሚ የምሆነው?

የሲዳማ የክልል ጥያቄ እነርሱ እንደምሉት የግለሰቦች ጥያቄ ሳይሆን የሰፊው የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ መሆኑን በግልጽ ኣይደለም ባሉበት ሚዲያ ቀርበው የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ መሆኑን እስክያረጋግጡ ድረስ የሲዳማ ህዝብ ከእነርሱ ጋር ምንም ኣይነት ውይይት የምያደርግ ኣይመስለኝም።

እንደምናውቀው የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ እና ፍላጎት የኣስተዳዳር ኣከባቢውን በክልል ደረጃ ማስተዳደር ነው። የሲዳማ ህዝብ ለዚሁ ዓላማ ላለፉት ከሰላሳ በላይ ዓመታት ልጆቱን መስዋዕት ኣድርጓል በማድረግም ላይ ነው። ታዲያ የህዝቡ ፍላጎት የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር መነጠቅ ሳይሆን ከዛም ባለፈ የራሱን ክልላዊ ኣስተዳደር መመስረት ነው። የህዝቡ ፈላጎት ይህ በሆነበት በኣሁኑ ወቅት ይህ መሰል የህዝቡን ፈላጎት ያላገናዘበ ውሳኔ መውሰድ የሲዳማ ህዝብ ፋላጎት እና ጥቅም ከማስጠበው ይልቅ የደኢህዴንን ፈላጎት ማስጠበቅ ነው።

ደኢህዴን የሲዳማን ህዝብ ፍላጎት እና ጥቅም ካላስጠበቀ ለሲዳማ ህዝብ ምኑ ነው? እኔ እንደማስበው ከሆነ በየትኛው ዓለም የምገኙት መንግስታት እና የፖለቲካ ድርጅቶች የቆሙላቸውን ህዝብ ፈላጎት እና ጥቅም ለማስጠበቅ ቀን ለሌት ስሰሩ ነው የምታዩ እንጂ በየትኛውም ኣጋጣም ከወከለው ህዝብ በተቃራኒ የቆሞ ድርጅት በታሪክ የለም ከደኢህዴን በስተቀር ማለት ነው። ደኢህዴን ከውሳኔ በኃላ ህዝቡን በውሳኔያቸው ላይ ለማወያያት ዳርዳር እያለ ነው። ተሳክቶላቸው እንኳን ህዝቡን ማሰባሰብ ከቻሉ፤ እኔ ኣሁን እያጓጓኝ ያለው የሲዳማ ኣመራሮች ያሳለፉት ውሳኔ የሲዳማን ህዝብ እንዴት ልጠቅም እንደምችል ለህዝቡ ቀርበው የምያብራሩበት ጊዜ ነው።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር