በፍርድ ቤቶች የሚሰጡ ውሳኔዎች የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶችን ስምምነት ያገናዘቡ ሊሆን እንደሚገባ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሀዋማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመለከተ፡


ጽህፈት ቤቱ አሥር ዋና ዋና አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነት ያካተተ  4ዐዐጥራዝ ለክለሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስረክቧል፡፡
ኢትዮጵያ ፊርማ ያፀደቀቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነት በሀገራዊ ቋንቋዎች መተርጐም ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በማቋቋሚያ አዋጅ ከተሰጡት ስልጠንና ተግባራት መካከል አንዱ ነው፡፡
ሰነዶቹ ለትምህርት ቤቶችና ለፍርድ ቤቶች እንዲሁም ለህግ ባለሙያዎች እንዲያገለግሉ ለማድረግ ኮሚሽኑ በአገራዊ ቋንቋዎች የመተርጐምና የማሰራጨት ሥራውን በቀዳሚነት እየሠራ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሀዋሣ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የመምርመራ፣ ጥበቃና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አታሮ እንደገለፁት የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ሰነዶች በአገራዊ ቋንቋ አለመተርጐምና በስፋት አለመሰራጨት ለሰነዶቹ አለመፈፀም ትልቅ ተግዳሮት ሆኖ ቆይቷል፡፡

ኮሚሽኑ ችግሩን ለመቅረፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት ሁሉን አቀፍ የሰብአዊ መብት መግለጫ፣ የህፃናት  እና የአካል ጉዳተኞችን መብቶችና ደህነንት ስምምነት ጨምሮ የተተረጐሙ አሥር ዋና ዋና አለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነት ሰነዶችን በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ፍርድ ቤቶች አገልግሎት እንዲሰጡ 4ዐዐ ጥራዞችን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስረክበቧለ፡፡
ስምምነቱን በማሳወቅና በሥራ ላይ እንዲውሉ በማድረግ በኩል የፍትህ አካላት የላቀ ሚና መጫወት እንደሚጠበቅባቸው አቶ ብርሃኑ አስገዝንበዋል፡፡
ሰነዶቹን የተረከቡት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት ተወካይ አቶ ሲሳይ ገመቹ በበኩላቸው የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ስምምነቶችና ድንጋጌዎች ተተርጐመው መሠራጨታቸው ዜጐች መብቶቻቸውን በአግባቡ የሚያውቁበትን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገለፀዋል፡፡
የሰነደቹ ሥርጭት መስፋፋት በተይም በፍርድ ቤቶች ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ግንዘቤ አንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡
አብዛኛዎቹ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች ትኩረት የሚያደርጉት በዋና ህጐች ላይ መሆኑን የገለፁት አቶ ሲሳይ የሰብአዊ መብቶች ሰነድ መዘጋጀቱ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱን የተሻለ እንደሚያደርገውም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ሰነዶቹን እስከታችኞቹ ፍርድ ቤቶች ድረስ ተደራሽ የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ተወካዩ የጠቆሙት፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/30MesTextN905.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር