በገጠር የተደራጀ የጠና ልማት ሰራዊት ለመገንባት በተደረገው ጥረት የጤና አክስቴንሸን ፖኬጅ ሙሉ በሙሉ በመተግበር ስኬታማ ለውጥ እየታየ እንደሚገኝ በሲዳማ ዞን የሁላ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡


የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታደሰ ካቢሶ እንደገለፁት በወረዳው ከ15ዐ  ሺህ በላይ አርሶ አደሮች 16ቱን የጤና ፓኬጆችን በግል፣ በቤተሰብ እንደዚሁም በህብረተሰብ ደረጃ ተግባራዊ በመደረጉ የተገኘው ውጤት አበረታች ነው፡፡
በአካባቢ ጤና አጠባበቅና በቤተስብ ጤና እንክብካቤ እንዲሁም ዋና ዋና ተላላፊ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር እንደተቻለም ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

የሁላ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የሲቪል ሰርቪስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተረፈ ዳሞታ በበኩላቸው በወረዳው የተጀመረው የጤና ልማት ሠራዊት ግንባታ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን እውን ለማድረግ የበኩሉን የሚወጣ ጤናማ ህብረተሰብ ለመፍጠር የሚያበረክተው አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የዞኑ ጤና መምሪያ ተወካይ አቶ ቃሪሳ ዳፉርሳ እንዳሉት በዞኑ የጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራም ትግበራው ውጤት እየተመዘገበ በመሆኑ ቀጣይነት እንዲኖረው ክትትልና ድጋፍ ከባለሙያና አመራሩ ይጠበቃል ብለዋል ሲል የሲዳማ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር