በመንግስት መስሪያ ቤቶች የተደራጀ የለውጥ ሰራዊት በመፍጠር የ5 ዓመቱን የልማትና የትራንስፎሜሽን እቅድ ማሳካት እንደሚቻል በሲዳማ ዞን የአሮሬሳ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡


በመንግስት መስሪያ ቤቶች የተደራጀ የለውጥ ሰራዊት በመፍጠር የ5 ዓመቱን የልማትና የትራንስፎሜሽን እቅድ ማሳካት እንደሚቻል በሲዳማ ዞን የአሮሬሳ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ወራና እንደተናገሩት ዘመናዊ  የሰው ሀይል በመገንባት መስሪያ ቤቶች መልካም አስተዳዳር ማስፈን እንደሚገባ ገልፀው ሁሉም ባለሙያ በተመደቡበት የስራ መስክ ውጤት ለማምጣት መጣር እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

የወረዳው ሲቪል ሰርቪስ ጽህፈተ ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ድኬ በበኩላቸው በመንግስት ሠራተኛው በፖለቲካዊ ፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስክ የለውጥ ሰራዊት ሆኖ በተመደቡበት ቦታ ግንባር ቀደም መሆን እንዳለበት ጠቁመው ለሠራተኛው የስራ ተነሳሽነት፣ ቅልጥፍናና በብቃት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ከሰልበጣኞች አንዳንዶች በሰጡት ሀሳብ ስልጠናው የተሻለ ግንዛቤ እንደጨበጡና በመንግስት መመሪያና ደንብ መሠረት በመስራት የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ሲል የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር