የኢትዮጵያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከ31 አመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈ



አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ)  የኢትዮጵያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለ2013ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ዛሬ ከሱዳን አቻው ጋር ባደረገው  የመልስ ጨዋታ ሁለት ለባዶ በማሸነፍ ከ31 አመታት ቆይታ በኋላ የአፍሪካ ዋንጫን ተቀላቀለ።
10 ሰአት ላይ በተጀመረው በዚህ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ65ኛው እና በ70ኛው ደቂቃ በአዳነ ግርማ እና ሳላዲን ሰኢድ ባስቆጠራቸው  ጎሎች ሁለት ለባዶ በማሸነፍ በደቡብ አፍሪካ ለሚካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን አረጋግጧል።
በዛሬው ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በርካታ የግብ ማግባት እድሎችን ቢፈጥርም ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል።
በመጀመሪያ ጨዋታው ሱዳን ላይ 5 ለ3  ቢሸነፍም  በድምር  ውጤት 5 እኩል  ሆነው ከሜዳው ውጭ ባገባው ጎል አላፊ ሆኗል።
ሰሞኑን ልምምዱን በኬኒያ ሲያደርግ የቆየው የሱዳን ብሄራዊ ቡድንም አርብ ምሽት አዲስ አበባ በመግባት ትናንት ቀለል ያለ ልምምድ ሲያደርግ ነበር።
በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በኩል ግብ ጠባቂው ጀማል ጣሰው ተጎድቶ በመውጣቱ እና ቡድኑ ተቀያሪ ተጫዋቾችን በሙሉ ተጠቅሞ በመጨረሱ ፥ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው አማካዩ አዲስ ህንጻ  የጀማልን ቦታ ሸፍኖ ቡድኑ በ10 ልጅ ጨዋታውን ለመጨረስ ተገዷል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር