ከ2ዐዐ2 ዓ/ም ጀምሮ በደቡብ ክልል ምክር ቤት አባልነት ሲያገለግሉ የቆዩት የተከበሩ አቶ ሀይሌ ባልቻ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡


ክቡር አቶ ኃይሌ ባልቻ ከወጣትነት እድሜያቸው ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማዎች የተመራውን ፀረ ፊውዳላዊ ተቃውሞ በወቅቱ የነበሩ የይርጋዓለም ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችም በትግል አጋርነት እንዲቀላቀሉ አስተባባሪ በመሆን መርተዋል፡፡
ክቡር አቶ ሀይሌ ባልቻ በደርግ ዘመን በ1997 ዓ/ም በተካሄደው ብሔራዊ ሸንጎ ምርጫ በጎርቼ ምርጫ ክልል በእጩነት ቀርበው የደርግ ሥርዓት እስከ ተወገደበት እስከ 1983 ዓ/ም ድረስ የመርጣቸው ህዝብ መብት መከበር የበኩላቸውን ድርሻ ማበርከታቸውን የህይወት ታሪካቸው ይገልፃል፡፡
በማህበሪዊ ህይወታቸውም የስኳር በሽታ ህሙማን የሆኑና ከፍለው መታከም የማይችሉ የሀዋሣና የአካባቢው ታማሚዎችን በማስተባበር የስኳር ህሙማን ማህበር በማቋቋም የህክምና እርዳታና ስለ በሽታው ግንዛቤ እንዲያገኙ በጎ ተግባርን ፈፅመዋል፡፡

በቤተሰብ ህይወታቸውም ሴት ልጅን በማስተማር በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ እንደ መልካም አርአያ ይቆጠሩ አንደነበር የህይወት ታሪካቸው ያመለክታል፡፡
የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ጥቅምት 12/2ዐዐ5  ሲፈፀም ሥነ ሥርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጨምሮ የከልል፣ የሲዳማ ዞንና የሀዋሣ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል፡፡
ክቡር አቶ ሀይሌ ባልቻ ባለትዳርና የ6 ወንድና የ4 ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡ የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች እንደዘገበው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር