በደቡብ ክልል ከተገነቡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አብዛኛዎቹ አገልግሎት ጀመሩ

አዋሳ ጥቅምት 14/2005 በደቡብ ክልል በ240 ሚልዮን ብር እየተገነቡ ካሉ 50 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል 46ቱ ተጠናቀው አገልግሎት መጀመራቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡ የቢሮው የመንግስት ኮሙኒኬሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አዳነ ንጉሴ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በክልሉ የምዕተ ዓመቱን የትምህርት ልማት ግቦች ለማሳካት ለተገነቡት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የውስጥ ድርጅት በማሟላት አገልገሎት ጀምረዋል፡፡ ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልገሎት ከበቁ ትምህርት ቤቶች መካከል 32ቱ ከ9ኛ እስከ 10ኛ ቀሪዎቹ የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ ግንባታው የአስተዳደር ቢሮ፣ ቤተ ሙከራ፣ ቤተ መፃህፍትና የመፀዳጃ ቤቶችን ያካተተ ነው ብለዋል፡፡ የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ በአብዛኛው የተከናወነው ቀደም ሲል 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ባልተዳረሰባቸው ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች መሆኑን የገለጹት አቶ አደነ በዚህ አካባቢ የሚታየውን የተሳትፎ ልዩነት ለማሻሻል እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡ ትምህርት ቤቶቹ ለአገልገሎት መብቃታቸው በክልሉ 287 የነበረውን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ወደ 333 በማሳደግ ከ22ሺህ ለሚበልጡ ተጨማሪ ተማሪዎች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡ በተለይ ሴቶች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ከመረዳቱም ባሻገር በትምህርት ቤትና በመኖሪያ አካባቢ መካከል ባለው ርቀት ምክንያት የሚደረሰውን ችግር የሚያስቀርና አቅም የሌላቸው ወላጆችን ችግር በእጅጉ እንደኒፈታ ገልጸዋል፡፡ በ2004 የትምህርት ዘመን አንድ ለ 66 የነበረውን የተማሪ ክፈል ጥምርታን ወደ አንድ ለ 60 ለማድረስ በመቻሉ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ አዲስ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ ትምህርት ቤቶች ከ87 ሚልዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመማሪያና ማስተማሪያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶች የማሟላት ስራ መከናወኑን አቶ አዳነ አብራርተዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=2935&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር