በሲዳማ ዞን ባፈው የክረምት ወራት ከ111 ሺህ በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት...፡



በሲዳማ ዞን ባፈው የክረምት ወራት ከ111 ሺህ  በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ 3 ሚሊዮን የሚጠጋ የመንግስት በጀት ከወጪ ማዳናቸውን የዞኑ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ አስታወቀ፡፡

በመምሪያው የወጣቶች ዘርፍ በ2ዐዐ4 እቅድ አፈፃፀምና በ2ዐዐ5 እቅድ ትግበራ ዙሪያ ሰሞኑን ውይይት አካሂደዋል፡፡

በዚህን ወቅት የመምሪያው ምክትልና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ ሳሙኤል እንዳሉት ወጣቶቹ በተለያዩ የማህበረሰብ ልማት ሥራዎች በመሳተፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ አድርገዋል፡፡

በአካባቢ ልማትና በአፈር ጥበቃ ብቻ ከ5 ሺህ 5ዐዐ በላይ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡


በሌላ በኩል በፓኬጅ ለተደራጁ ወጣቶች ከተሰራጨው ከ13 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ የብድር ገንዘብ 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር እንዲመለስ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

ይሁንና አፈፃፀሙ ከግማሽ በታች ነው ያሉት ምክትል ኃላፊው ለዚህም በምክንያነት የሚጠቀሱት የተሰጠው ብድር ሳይመለስ በወቅቱ የነበሩ ኃላፊዎች መቀያየር እንዲሁም አንዳንድ ወጣቶች ገንዘቡ የማይመለስ አድርገው መመልከትና ጉዳዮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ ያለመሥራት ናቸው ብለዋል፡፡ ዘገባው የሲዳማ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/9TikTextN405.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር