የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ ነገ ይሰበሰባል


አዲስ አበባ ነሐሴ 28/2004 የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ ነገ ማክሰኞ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡ በነገው ዕለት በሚከፈተው የግንባሩ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃጸምን ይዳስሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ኮሚቴው የ2004 በጀት ዓመት አፈፃጸሞችን በጥልቀት በመፈተሽ የግንባሩ ሊቀመንበር የነበሩትና የባለ ራዕዩና ታላቁ መሪ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ በሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተስተጋባውን ቁጭትና እልህ በልማት ላይ በሚቻልበት ሁኔታ እንደሚነጋገር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የታላቁን መሪውና በእሳቸው የተገነባውን የግንባሩና የአገሪቱ ልማታዊ መንግሥት ራዕይ ሁሉም በየተሰማራበት የስራ መስክ በመረባረብ ለማስቀጠል የገባውን ቃልና መነሳሳት የሚመጥን ዝግጅት ማድረግ በሚቻልባቸው ዙሪያም ኮሚቴው ይመክራል፡፡ በተጨማሪም ከኮሚቴው አባላት በሚነሱ አጀንዳዎች ዙሪያ በመምከር ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል ሲል ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡

http://www.ena.gov.et/story.aspx?ID=2329

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር