ኢህአዴግ አጣብቂኝ ውስጥ

የኢህአዴግ ስራአስፈፃሚ ማክሰኞ፣ መሰከረም 4፣ 2012 ተሰብስቦ ውሎአል። ስብሰባውን ባለማጠናቀቁም ዛሬ መስከረም 5 ቀጥሎ እንደሚውል መረጃዎች ይጠቁማሉ። የስራአስፈፃሚው አባላት በጥቅሉ 36 ሲሆኑ፣ በመለስ መሞት ምክንያት ተሰብሳቢዎቹ 35 ናቸው። 
  
ህወሃትን ወክለው በስብሰባው ላይ የተገኙት 8 ሰዎች፣ ፀጋይ በርሄ፣ አባይ ወልዱ፣ አባዲ ዘሙ፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ደብረፅዮን፣ በየነ እና አዜብ መስፍን ሲሆኑ፣ ነባሮቹ እና አንጋፋዎቹ የህወሃት አመራር አባላት ከስብሰባው ውጭ በመሆናቸው ኢህአዴግ በብአዴን እጅ ላይ መውደቁ ይነገራል። ከብአዴን በረከት ስምኦን እና አዲሱ ሲገኙ ከኦሮሚያና ከደቡብ ግርማ ብሩ እና ሬድዋን ሁሴን ተገኝተዋል። 8ቱ የህወሃት አባላት መለስን የሚተካ አንድ ሰው ወደ ስብሰባው ለመጨመር ጠይቀው የአመራሩ አባላት አሰራሩን በመጥቀስ ሳይፈቅዱላቸው ቀርተዋል። 

ትናንት በዋለው ስብሰባ ላይ ሙሉ መግባባት ላይ ሊደርሱ ባለመቻላቸው፣ አጀንዳቸውን ለማሳደር ተገደዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የስራአስፈፃሚው ስብሰባ ላይ መሳተፍ ያልቻሉት አንጋፋዎቹ የህወሃት አመራር አባላት ድርድር ጠይቀዋል። እነዚህም፣ ስዩም መስፍን፣ አርከበ ኡቅባይ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ፣ ስብሃት ነጋ እና ሳሞራ የኑስ ናቸው።

አከራካሪው አጀንዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የምክትሉ ሹመት ጉዳይ ሲሆኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታም እንዲሁ እያወዛገበ ይገኛል። 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር