ኢራፓ በፓርቲዎችና በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው አፈና እንዲቆም ጠየቀ


መንግሥት በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በጋዜጠኞችና በሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ላይ የሚያደርሰውን አፈና እንዲያቆም የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ጠየቀ፡፡በአገሪቱ የሚታየውን ሙስና ለማጥፋት ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ህብረተሰቡ ከመንግስት ጐን መሰለፍ አለባቸው ብሏል - ፓርቲው፡፡የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ተሻለ ሰብሮ ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ቁርሾ፤ ቂምና በቀል በማስወገድ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ  የመፍትሄ አማራጮችን ማፍለቅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ በጋዜጠኞችና በሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ላይ የሚደርሰው አፈና እንዲቆም ሊ/መንበሩ ጠይቀዋል፡፡ ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚዎች፤ እንዲሁም ተቃዋሚዎች እርስ በእርስ በአገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ላይ የሚነሱ ችግሮችን በመመርመር በጋራ መፍትሄ ሊሰጡ ይገባል ብለዋል - አቶ ተሻለ ሰብሮ፡፡ በሚዲያ ነፃነትና በኑሮ ውድነት ዙሪያ ፓርቲዎች በጋራ ተወያይተው መፍትሄ እንዲሰጡም የፓርቲው ሊ/መንበር ጥሪ አቅርበዋል - በፓርቲው ፅ/ቤት በሰጡት መግለጫ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር